የአማራክልል አጠቃላይ ሁኔታ

የአማራ ብሄራዊ ክልል ጅኦግራፊያዊ አቀማመጥ በ80 45’ እስከ 130 45’ ሰሜን የኬክሮስ እና በ350 46’ እስከ 400 25’ ምስራቅ የኬንትሮስ መስመር ዉስጥ የሚገኝ ሲሆን አዋሳኞቹም በሰሜን ተግራይ፣ በምስራቅ አፋር፣ በደቡብ ኦሮሚያ፣ በምዕራብ ደቡብ ቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልልና ምዕራብ ሱዳን ናቸዉ፡፡ በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ  (CSA) መረጃ መሰረት ክልሉ 168,966 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ያለዉ ሲሆን ይህም ከአገሪቱ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት ዉስጥ 15% ያህሉን  ይሸፍናል፡፡

በክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የህዝብ ቁጥር ትንበያ (Demographic Projection) መሰረት በ2006 ዓ.ም የክልሉ ህዝብ 20, 019,090 (ወ=10,011, ሴት=10,007,249) እንደሚደርስ የተገመተ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 16,892,093 (84%) በገጠር የሚኖር ህዝብ ሲሆን ቀሪዉ 3,126,9977 (16%) በከተማ የሚኖር ነዉ፡፡ የክልሉ አስተዳደራዊ መዋቅር ሲታይ በ7 የዞን አስተዳደሮችና በ3 የብሄረሰብ አስተዳደሮች፣ በ167 የከተማና የገጠር ወረዳዎች እና በ3,600 የከተማና የገጠር ቀበሌዎች የተዋቀረ ሲሆን የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የአዊ፣ የዋግ ኸምራና የአርጎባ ህዝቦች በጋራና በወንድማማችነት የሚኖሩበት ክልል ነዉ፡፡

የመሬት አቀማመጥ፣ የአየር ንብረትና የአፈር አይነቶች

የክልሉ የመሬት አቀማመጥ ሜዳማ (37.60%) ተራራማ (27.79%)፣ ጥልቅና ሰፋፊ ሸለቆዎች (11.40%) እና ረግረግ መሬቶች (1.45%) ሲሆን የከፍተኛ ቦታዎች ምድብ የሚይዘዉ ከባህርዳር ወለል በላይ ከ1500 መሬት በላይ የሆኑትን ቦታዎች ሰንሰለታማና አምባ ምድሮች፣ እንደ ራስ ዳሽን (4620 ሜትር)፣ አቡነ ዮሴፍ (4290) የመሳሰሉት ትልልቅ ተራራዎችን የሚያቅፍ ነዉ፡፡ የዝቅተኛ ቦታዎች ምድብ ደግሞ የክልሉን ምዕራባዊና ደቡባዊ ቦታዎች የሚያቅፍ ሲሆን ከባህር ወለል በላይ ያላቸዉ ከፍታ ከ500-1500 ሜትር ነዉ፡፡ ይህ ምድብ የትልልቅ ወንዞችን፣ ተፋሰሶች የሚሸፍንና ሜዳማ የሆነ የመሬት አቀማመጥ ያለዉ በመሆኑ ሰፋፊ እርሻዎችን ለማካሄድ አመቺነት ያለዉ አካባቢ ነዉ፡፡

 

ክልሉ በ4 ዋና ዋና የአየር ንብረቶች የተከፋፈለ ሲሆን 33.66% ቆላ፣ 20.37% ያህሉ ደጋ፣ 45.14% ወይና ደጋ፣ 0.83% ያህሉ ደግሞ ዉርጭ የአየር ንብረት አለዉ፡፡ የክልሉ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ27.8 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ሲሆን ዝቅተኛዉ ከ12.4 ዲግሪ ሴንቴግሬድ በታች ይወርዳል፡፡ የክልሉ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ዝቅተኛዉ ከ500-700 ሚ/ሜትር ሲሆን ከፍተኛዉ ደግሞ ከ1400 ሚ/ሜትር በላይ ይደርሳል፡፡

በክልሉ ዉስጥ በርካታ የአፈር ዓይነቶች እንዳሉ ቢታወቅም በአብዛኛዉ የተለመዱትና ለልዩ ልዩ አዝዕርት ልማት በተስማሚነታቸዉ የሚታወቅ ቀይ (30.4%1)፣ ቡናማ (24.90%)፣ ጥቁር (32.05%)፣ ግራጫ (11.12%) እና ሌሎች 1.52% የመሬት ሽፋን ድርሻ አላቸዉ፡፡

Social sector Bureau