የመስሪያ ቤቱ ስም - የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት

ተልዕኮ

ሕገ መንግስቱን፣ሰብዓዊ መብትን እና ሕግ ማክበርና ማስከበር፤ወንጀል በመከላከልና የወንጀል ሕግን በማስከበር የሕዝብ፣የመንግስት እና የግለሰቦች ሠላም ደህንነት ማረጋገጥ፤የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ማስጠበቅ፤የህብረተሰቡን ንቃተ ሕግ ማሳደግ፤ተደራሽ፣ቀልጣፋ፣ፍትሃዊና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት መስጠት፡፡

ራዕይ

በ2022ዓ.ም ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የተከበረበት፤የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበት፤ፍጥሕ የሰፈነበት ብሔራዊ ክልልን በመፍጠር ለተምሳሌትነት የሚበቃ ተቋም ሆኖ ማየት፣

ስልጣንና ተግባር

 1. በፌደራልመንግሥቱ ተዘጋጅቶ የፀደቀውን የወንጀል ፍትህ ፖሊሲ በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን ይሰራል፣ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
 2. በክልሉ ውስጥ የወንጀል ፍትሕ መረጃዎችን ለመሰብሰብ፣ ለማደራጀት፣ ለመተንተንና ለማሰራጨት የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያስፈፅማል፤
 3. በሕግጉዳዮች ረገድ የክልሉ መንግሥት ዋና አማካሪ ሆኖ ይሰራል፤
 4. የዓቃቤ-ሕግ የውሳኔ አሰጣጥና የፍቅደ-ሥልጣን አጠቃቀም ወጥነትን ለማረጋገጥ በፌደራሉ ጠቅላይ ዓቃቤ-ሕግ መስሪያ ቤት የፀደቀው መመሪያ በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ መደረጉን ያረጋግጣል፤

 

 1. ዓቃብያነ-ሕግ የሚያሳልፏቸው ውሳኔዎች በሕግ መሰረት መሰጠታቸውን የሚያረጋግጥ የክትትልና የቁጥጥር ማከናወኛ ክፍል ያደራጃል፣ ጉድለቶችን በጥናት ላይ ተመስርቶ ይለያል፤ በግኝቱ መሠረትም የእርምት እርምጃዎችን ይወስዳል ወይም በሌሎች አካላት እንዲወሰዱ ያደርጋል፤

 

 1. አግባብካላቸው አካላት ጋር በመተባበር በትርፍ ላይ ያልተመሠረተ ዓላማ ይዘው የተቋቋሙናበክልሉ ውስጥ የሚንቀሣቀሱ ማህበራትን፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንና የሀይማኖት ተቋማትን ሕጋዊነት በማረጋገጥ ይመዘግባል፣ ይቆጣጠራል፣ ይሰርዛል፤

 

 1. ከዚህ በላይ ከንዑስ አንቀጽ (1) እስከ ንዑስ አንቀጽ (6) ድረስ የሰፈሩት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው የወንጀል ጉዳዮችን በተመለከተ፡-

 ሀ) በሌላ ሕግ ለክልሉ የገቢዎች ባለስልጣን የተሰጠው የአቃቤ-ሕግነት ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በክልሉም ሆነ በፌደራሉ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ስር የሚወድቅና በፖሊስ የተጀመረ የወንጀል ምርመራ ቢኖር አስቀድሞ እንዲያውቀው መደረግ ያለበት ሲሆን የምርመራ አካሄዱን ህጋዊነት ይከታተላል፣ ይመራል፣ በተጀመረየወንጀል ምርመራ ላይ ሪፖርት እንዲቀርብና ምርመራው በአግባቡ ተከናውኖ እንዲጠናቀቅ ያደርጋል፤

ለ) በሕዝብ ጥቅም መነሻነት ወይም በወንጀል የማያስጠይቅ ሁኔታ መኖሩ በግልፅ ሲታወቅ የወንጀል ምርመራ እንዲቋረጥ ወይም የተቋረጠ የወንጀል ምርመራ እንዲቀጥል ሊያደርግ ይችላል፣ ምርመራውበሕግ መሰረት መከናወኑን ያረጋግጣል፣ ከነዚሁ ተግባራት ጋር በተያያዘም ለፖሊስ ወይም ወንጀል ለመመርመር ሥልጣን ለተሰጠው ሌላ አካል አስፈላጊውን ትእዛዝ ይሰጣል፤

ሐ) በምርመራ መዛግብት ጥናትና ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ከፖሊስ በኩል ተፈላጊውን ድጋፍ ሊጠይቅ ይችላል፣ በወንጀል መዛግብት ላይ የተሰጡ የዓቃቤ-ሕግና የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ለሚመለከተው ፖሊስ ያሳውቃል፣ የወንጀልምርመራ መዛግብትን አስመልክቶ በየደረጃው ዓቃብያነ-ሕግ በተሰጡ ውሳኔዎች ላይ በፖሊስ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያጣራል፣ ውሳኔዎችን ይሰጣል፤

መ) በየደረጃው የሚገኝ ዓቃቤ ሕግ በትይዩ ባሉት ፍርድ ቤቶች ጉዳዮችን በከሳሽነት ይዞ የመከራከር መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በስር ዓቃብያነ-ሕግ የተሠጡ የክስ አያስቀርብም ውሳኔዎችን ይመረምራል፣ ግድፈት ያጋጠመው እንደሆነም ወዲያውኑ እንዲታረም ያደርጋል፣ የተጠናቀቁየምርመራ መዛግብትን ከማስረጃ እና ከሕግ አንፃር መርምሮ የአያስከስስም ውሳኔ ይሰጣል፤

ሠ) የእጅ ተፍንጅ ወንጀሎች ተፈፅመው ሲገኙ በተፋጠነ ሥነ-ሥርዓት ውሣኔ የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቻል፣ ለዚህም ከፖሊስና ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ ይሠራል፤

ረ) ለወንጀል ጉዳይ ምስክሮች በወቅቱ መጥሪያ እንዲያደርስና ምስክሮችንም ወደ ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ ለፖሊስ ትእዛዝ ይሰጣል፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘውም የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያገኙ ያደርጋል፤

 

ሰ) የጥፋተኝነት ድርድር እንዲካሄድ ይወስናል፣ ድርድር ያደርጋል፣ አማራጭ የመፍትሄ እርምጃ እንዲወሰድ ይወስናል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤

ሸ) በግብር እና ታክስ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በተመለከተ ለክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን በሌላ ሕግ የተሰጠው የአቃቤ-ሕግነት ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ የክልሉን መንግሥት በመወከል በወንጀል ጉዳዮች ክስ ይመሰርታል፤ ይከራከራል፣ ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ክስ ያነሳል፤ የተነሳ ክስ እንዲቀጥል ያደርጋል፤ ሆኖም ጉዳዩ በልዩ ሁኔታ ክልላዊ ይዘት ያለው ሆኖ ሲገኝ ርዕሰ-መስተዳድሩን በማማከር ክስ ስለሚነሳበት ሁኔታ መመሪያ ያወጣል፤

 ቀ) ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ የሚሰጧቸው ውሳኔዎችና ትዕዛዞች መፈፀማቸውንና መከበራቸውን ይከታተላል፣ ሳይፈፀሙ ከቀሩ ወይም አፈፃፀማቸው ሕግን ያልተከተለ ከሆነም በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለሰጠው ፍርድ ቤት በማመልከት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤

በ) በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የወንጀል ቅጣቶች በአግባቡ እንዲፈፀሙ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥርዓቶችን ያደራጃል ወይም መደራጀታቸውን ያረጋግጣል፤

ተ) የሞት ቅጣት ውሳኔዎችን ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ፕሬዚደንት ያቀርባል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፡፡

8. የፍትሐብሔርጉዳዮችን በተመለከተ፡-

ሀ) የክልሉ ህዝብና መንግሥት መብቶችና ጥቅሞች ህጋዊ ወኪል በመሆን ይደራደራል፣ይከራከራል፣ ያስከብራል፣ እንዲከበሩ ያደርጋል፣ የሚከበሩበትን ሂደት ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤

ለ) የክልሉ መንግሥት ተቋማት ሀብትና ንብረት ያለአግባብ እንዳይባክንና እንዳይመዘበር ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤

ሐ) ይህንን አዋጅ ተከትሎ በሚወጣ ደንብ በሚወሰነው መሰረት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በክልሉ መንግሥት ፕሮጀክቶች ላይ የውል ዝግጅትና ድርድሮችን ያካሂዳል፣ የክልሉ መንግሥት መስሪያ ቤቶችና የህዝብ መብትና ጥቅም ይጎዳል ብሎ ሲያምን በሌሎች ጉዳዮች ጭምር የውል ሰነዶች ዝግጅትና ድርድር ያደርጋል ወይም የሚመለከታቸውን አካላት ያማክራል፤

መ) ከክርክርበፊት፣ በክርክር ወቅት   እንዲሁም ከክርክር  በኋላ  አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመንግስት መስሪያ ቤቶች ምክር ይሰጣል፣ አቅጣጫዎችን ያሳያል፣ በሕግ መሰረት ውሳኔዎችን ያስፈፅማል፤

ሠ) ከስር አቃብያነ-ሕግ በሚላኩለት ወይም በሚቀርቡለት የፍትሀ-ብሄር መዛግብት ላይ የክስ አይቀርብም ውሳኔዎችን  ይሰጣል እንዲሁም የስር አቃቤ-ሕግ በሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ሲቀርብለት ወይም በራሱ አነሳሺነት ውሳኔውን መርምሮ ያፀናል፣ ይሽራል ወይም ተለዋጭ ትዕዛዝ ይሰጣል፤

 

ረ) በየደረጃው ያለ ዓቃቤ ሕግ በትይዩ ባሉት ፍርድ ቤቶች በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት ጉዳዮችን ይዞ እንዲከራከርና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ደረጃውን ሳይጠብቅ ጉዳዩን ተረክቦ እንዲሟገት ያደርጋል፤

ሰ) ዝርዝሩ ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም ወደፊት በሚወጣ ደንብ ወይም መመሪያ የሚወሰን ሆኖ የክልሉ መንግሥት መስሪያ ቤቶች አንደኛው ከሌላው ጋር ያልተግባቡባቸው የፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች ያጋጠሙ እንደሆነ እርስ በርስ በማደራደር የመጨረሻ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ይረዳል፣ አፈፃጸሙን በቅርብ ይከታተላል፤

በልዩ የሥራ ጠባያቸው ምክንያት የራሣቸው ነገረ-ፈጅ ካላቸው መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ውጭ ያሉትን ክልላዊ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በመወከል በፌደራልና በክልል ፍርድ ቤቶች፣ በማናቸውም የዳኝነት ሰሚ አካል ወይም የሽምግልና ጉባኤ ፊት ክስ ይመሠርታል፣ ሲከሰሱም መልስ ይሰጣል፣ ይደራደራል፣ ይከራከራል፤

 

ቀ) በልዩ ሁኔታ የራሣቸው ነገረ-ፈጅ ያላቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ተከራካሪ በሚሆኑባቸው የፍትሐብሔር ክሶችና የመብት ጥያቄዎች ዙሪያ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን ያከናውናል፣ የሕግ ድጋፍ ሲጠየቅ እገዛ ያደርጋል፤

በ) በሕግ ከተወሰነው የገንዘብ መጠን በላይ በሆኑ ጉዳዮች የህብረት ሥራ ማህበራትን በመወከል ሲከሱም ሆነ ሲከሰሱ ይከራከራል፣ ይደራደራል፣ እንዳስፈላጊነቱ ሌሎች የሕግ ድጋፎችን ይሰጣል፤

    ተ) በወንጀል ድርጊት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውንና ገንዘብ ከፍለው መከራከር የማይችሉ አቅም የሌላቸው ሰለባዎች፣ የአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህጻናት፣ ድሀ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ህሙማንን ወክሎ በድርድር ወይም በክልሉ ፍርድ ቤቶችና በሌሎች የዳኝነት አካላት ዘንድ ክስ በመመስረትና በመከራከር እነዚሁ ወገኖች ካሣ እንዲያገኙና ፍትሐብሔር ነክ ጥቅሞቻቸው እንዲከበሩ ያደርጋል፤

 

 ቸ) በክልሉ መንግሥት መስሪያ ቤቶችና በሌሎች ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው የህብረተ-ሰብ ክፍሎች መካከል በሚነሱ የፍትሐብሔር ክርክሮች ጉዳዩን በድርድር ለመፍታት ጥረት ያደርጋል፤ በድርድር መፍታት ካልተቻለ የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን ጉዳይ ይዞ ይከራከራል፡፡

 

 1. የሕግ ምክር፣ ማርቀቅና ማጠቃለል በተመለከተ፡-

   ሀ) ከክልሉ መንግሥት ተቋማት የሚመነጩ የሕግ ሀሳቦችን ተቀብሎ ረቂቅ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን ያዘጋጃል፣ በሌሎች አካላት ተዘጋጅተው ሲቀርቡለት ጥራታቸውን ጠብቆ ያበለጽጋል፤

ለ) በክልሉ ውስጥ የተለያዩ አካላት የሚያዘጋጇቸው የሕግ ረቂቆችከሕገ-መንግሥቱም ሆነ ከክልሉና ከፌደራል መንግሥቱ ሕግጋት ጋር የተጣጣሙ ስለ መሆናቸው ይከታተላል፣ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከታቸው ክፍሎች ሙያዊ አስተያየት ያቀርባል፤

   ሐ) የክልሉ መንግሥት ሕጎች ተግባራዊ መደረጋቸውን እና አተገባበራቸውም ወጥነት ያለው መሆኑን ያረጋግጣል፣ እንዲሁም የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ሥራቸውን በሕግ መሰረት ማከናወናቸውን በቅርብ ይከታተላል፤

 

መ) በሥራ ላይ ያሉትን የክልሉን ሕጎች በየጊዜው እያጠና ወይም በሌሎች እያስጠና የሚሻሻሉበትን የውሳኔ ሃሳብ በማዘጋጀት ለክልሉ መንግሥት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ለማሻሻያዎቹ የሚያስፈልጉትን ረቂቆች በማዘጋጀት ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የሥልጣን አካላት አቅርቦ ያስጸድቃል፤

 

ሠ) የሕግ ጉዳዮችን በተመለከተ የክልሉን መንግሥት ተቋማት ያማክራል፤

 

ረ) ዓቃብያነ-ሕግ ስለ ሥራቸው ያላቸውን አመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት በተከታታይና በየደረጃው ለማሳደግ ይቻላቸው ዘንድ ተገቢውን የአቅም ግንባታ እንዲያገኙ ያደርጋል፤

 

ሰ) የሕግየበላይነትንለማረጋገጥለክልሉመንግሥትባለሥልጣናት፣ሌሎችተሿሚዎች፣

የህዝብተመራጮች፣

ሠራተኞችእንዲሁምየግሉዘርፍተሳታፊዎችእንዳስፈላጊነቱየንቃተ-ሕግመርሀ-ግብሮችንያዘጋጃል፣ይሰጣልወይምእንዲሰጥያደርጋል፤

 

 ሸ) የክልሉንናበክልሉውስጥተፈጻሚነትያላቸውንየፌደራልመንግሥትሕግጋት

የማሰባሰብናየማጠቃለልሥራዎችንያከናውናል፡፡

 1.  ሰብዓዊመብቶችንበተመለከተ፡-

 

      ሀ) የሰብዓዊመብትጥሰትንበተመለከተየሚቀርቡ

አቤቱታዎችንናቅሬታዎችን

ይመረምራል፣እንዲመረመሩያደርጋል፤

 

ለ) የክልሉመንግሥትመስሪያቤቶችእቅድየሰብዓዊመብትጉዳዮችን

ያካተተስለመሆኑ

በቅርብይከታተላል፣ይደግፋል፤

ሐ) ነፃየሕግድጋፍአሰጣጥስትራቴጂዎችንይቀርፃል፣አፈፃፀማቸውንይከታተላል፣

በመስኩየሚሰማሩአካላትንያስተባብራል፤

 

መ) ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በፌደራል ደረጃ የወጣው የብሔራዊ ሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሀ-ግብር በክልሉ ውስጥ ያለውን ተፈፃሚነት ይከታተላል፤ በክልል-አቀፍ ደረጃ ተሳታፊ የሚሆኑትን ወገኖች እንቅስቃሴዎች ያስተባብራል፤ አግባብ ላላቸው አካላት ሪፖርት ያቀርባል፤

 

ሠ) በፖሊስ ጣቢያና በማረሚያ ቤት ጥበቃና ቁጥጥር ሥር ያሉ ሰዎችን ይጎበኛል፣ አያያዛቸውና ቆይታቸው በሕግ መሰረት መከናወኑን ያረጋግጣል፣ እንዲሁም ሕግን ተላልፈዋል በተባሉ ሰዎች ላይ በሕግ መሰረት እርምጃዎችን ይወስዳል ወይም እንዲወሰዱ ያደርጋል፤

ረ) የክልሉ ህብረተ-ሰብ ሰብአዊ መብቶቹንና ግዴታዎቹን በውል ተገንዝቦ ሕግ አክባሪና አስከባሪ እንዲሆን በተለያዩ ዘዴዎች የሰብአዊ መብትና የንቃተ-ሕግ ትምህርት ይሰጣል፣ በዘርፉየተሰማሩ አካላትን እንቅስቃሴዎች ያስተባብራል፤

ሰ)ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው ወይም የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች በክልሉ ውስጥ ያላቸውን ተፈጻሚነት ይከታተላል፤

ሸ) እንደ ስርአተ-ጾታና ኤድስ ያሉ ዘርፈ-ብዙና ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተ-ሰብ ክፍሎችን ያካተቱ የሰብአዊ መብት ተግባራትን ያከናውናል፤

ቀ) ሰብዓዊመብትን የሚመለከቱ ፕሮጀክቶችን ያስተባብራል፣ ይደግፋል፣ ይከታተላል፤

በ) ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት በኩል ጥያቄ ሲቀርብለት ሀገሪቱ የተቀበለቻቸውን የሰብአዊ መብት ስምምነቶች ብሔራዊ የአፈፃፀም ሪፖርት በማዘጋጀት ረገድ ይተባበራል፣ ያግዛል፤

 

 1.  የጠበቆችአስተዳደርን በተመለከተ፡-

 

ሀ) በክልሉፍርድ ቤቶች ደረጃ የጥብቅና አገልግሎት ለሚሰጡ ጠበቆች በሕግ መሠረት ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤

 

ለ) የጠበቆችን አገልግሎት አሰጣጥ ይከታተላል፣  ይቆጣጠራል፤

 

ሐ) ለአደጋተጋላጭ የሆኑ ድሀ የህብረተ-ሰብ ክፍሎችን ፍትሕ የማግኘት መብት ለማስከበር የግል ጠበቆችን፣ የጠበቆች ማህበራትን ወይም ልዩ የጥብቅና ፈቃድ ያላቸውን የሲቪል ማህበራት በማስተባበር ነፃ የሕግ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡

 1. የሰነዶችምዝገባና ማረጋገጥን በተመለከተ፡-

 

ሀ) በክልሉ ውስጥ የሰነዶችን ሕጋዊነት ያረጋግጣል፣ ይመዘግባል፤

ለ) በተጭበረበረ ሰነድ ወይም ያለአግባብ የተረጋገጠና የተመዘገበ ሰነድ በሚገኝበት ጊዜ ይህንኑ ያግዳል፣ ያጣራል፣ ያለ አግባብ ተሰጥቶ ሲገኝም ይሠርዛል፡፡

 

 1.  የአገልግሎትአሰጣጥ፣ የቅሬታ ማስተናገጃና ስነ-ምግባር ክትትልን በተመለከተ፡-

ሀ) ቅድሚያየሚሰጣቸውን የደንበኞች ፍላጎቶች በጥናት በመለየት የአገልግሎት አሰጣጥ ስልት ይቀይሳል፤

 

ለ) በግልም ሆነ በወል የሚቀርቡ ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን ተቀብሎ ያጣራል፣ ፍትሐዊ ውሳኔዎችን ይሰጣል፤

 

ሐ) ይህንን አዋጅና በሥራ ላይ ያሉ ሌሎች ሕጎችን በመተላለፍ የዲሲፕሊን ጥፋት በፈጸሙ የየደረጃው አቃብያነ-ሕግና ጠበቆች ላይ እንደተገቢነቱ በአቃብያነ-ሕግ አስተዳደርም ሆነ በጠበቆች የዲሲፕሊን ጉባኤዎች ፊት የዲሲፕሊን ክስ ይመሰርታል፣ ይከራከራል፤

መ) ከዲሲፕሊንውሳኔዎች ጋር በተያያዘ ዓቃብያነ-ሕግንና ጠበቆችን አስመልክቶ መስሪያ ቤቱ በሰጣቸው ውሳኔዎች ላይ ለመደበኛ ፍርድ ቤቶች በሚቀርቡ የይግባኝ ጉዳዮች ላይ መልስ ይሰጣል፣ ፍርድ ቤት ቀርቦ ይከራከራል፤

ሠ) የመስሪያ ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የቅሬታ አቀባበልና የስነ-ምግባር ደንቦችና መመሪያዎች በሁሉም ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ዘንድ ተገቢውን ግንዛቤ አግኝተው በአግባቡ እንዲተገበሩ ለማስቻል ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፤

ረ) በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የለውጥ ፕሮግራሞችን ገቢራዊነትናየክልሉን ፍትሕሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራም ውጤታማነት በቅርብ ይከታተላል፡፡

 1.  አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሥልጣንና ተግባራቱን አስቀድሞ በሚዘረጋ የአፈፃፀም፣ የክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ ሥርዓት መሠረት ለሌሎች የክልሉ መንግሥት አካላት በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል፤
 2. በሕግ መሰረት የንብረትባለቤትና የይዞታ ባለመብት ይሆናል፣ ውሎችን ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል፣ ይከሰሳል፤
 3. ዓላማዎቹን ለማስፈፀም የሚረዱትንና በሌሎች ሕጎች የተሰጡትን ተዛማጅ ተግባራት ያከናውናል፡፡