Web Content Display Web Content Display

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

የሰላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ ታሪካዊ አመጣጥናአ መሰራረት የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳች ቢሮ በሚል ስያሜ በአዋጅቁጥር60/1994 ጀምሮ ተቋቁሞ የነበረው

Ø  ቢሮ በክልሉ ውስጥ ህግና ስርዓት መከበሩን እና የህዝብሰ ላምና ደህንነት መጠበቁን ማረጋገጥ፣

Ø  ህግ አስከባሪ አካላትን ዴሞክራሲያዊ አመለካከትና ሰብ-አዊ መብቶች ዙሪያ ግንዛቤ ማሳደግ፣

Ø  በክልሉውስጥእናአጎራባችክልሎችመካከልየሚነሱአለመግባባቶችንበሰላማዊመንገድመፍታት፣

Ø  የጸጥታ ተቋማትን አስተባብሮ መምራት እና ከሚመለከታቸው የፌደራል ተቋማት ጋር በመተባበር የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ መሰረት አድርጎ የተቋቋመና የሚሰራ ቢሮ ነበር፡፡

በዚህም መሰረት በክልሉ ውስጥ ህግና ስርዓት ለማስከበር፣ የህዝቦችን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥና የጸጥታ ተቋማትን ድጋፍ በማጠናከር የተለያዩ አስራርሥ ርዓት በመዘርጋት በክልሉ ውስጥ ስራዎች ሲሰሩ የቆዩ በመሆኑ የተቋሙ ዋና ተልዕኮው ሆኖ ቆይቷል፡፡

የክልሉን አስፈጻሚ አካላትን እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር176/2003 ዓ.ም የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ የሚለውን የቀድሞውን ስያሜ እንደያዘ ከድሮው በአዋጅ ቁጥር60/1994 ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት በተጨማሪ በትርፍ ላይ ያልተመሰረተ ዓላማ ይዘው የተቋቋሙና በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ማህበራት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሀይማኖት ተቋማት ህጋዊነት ከሚመለከተው አጋር አካላት ጋር በመተባበር እንዲሰራ፤ የህዝብ ግጭቶችን የመከላከል፣የመፍታት እና የማስተዳደር ተግባር እና ኃላፊነት ተሰጥቶት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ስለሆነም የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ፣ ህግና ስርዓትን በማስከበር፣ የዜጎችን ሰብ-አዊና ዴሞክራሲያ ዊመብቶችን በማስከበር፣ በክልሉ ውስጥና የአዋሳኝ ክልሎችን የህዝብ ግጭቶችን በመከላከልና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን የማጠናከር፣ ህገ-ወጥነትን በመከላከል፣ ተጠሪ ተቋማትን አስተባብሮ በመምራትና የተለያዩ ግብዓቶችን በማሟላት ከፌደራል የፀጥታ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት በተደረጉ ጥረቶች ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

ክልሉን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማትና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በፀጥታ ስጋት ምክንያት እንዳይደናቀፍ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ የክልሉን አስፈጻሚ አካላት አዋጅ ቁጥር176/2003 ዓ.ም የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ትርፍ ላይ ያልተመሰረተ ዓላማ ይዘው የተቋቋሙና በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ማህበራት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሀይማኖት ተቋማት ህጋዊነት ከሚመለከተው አጋር አካላት ጋር በመተባበር እንዲሰራ በአዋጅ ቁጥር264/2011 ዓ.ም አንቀጽ36/2/ለ/ መሰረት በሰላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ ተፈፃሚነት አንደማይኖራቸው ተደንግጓል፡፡

በመሆኑም የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉ አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባራት እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር264/2011 ዓ.ም ሰላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ተሰጥቶታት፡፡

read more