Web Content Display Web Content Display

"ሰላም የመልዕክት አብሳሪ ናት "  

 የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

የሰላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ ታሪካዊ አመጣጥናአ መሰራረት

የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳች ቢሮ በሚል ስያሜ በአዋጅቁጥር60/1994 ጀምሮ ተቋቁሞ የነበረው

Ø  ቢሮ በክልሉ ውስጥ ህግና ስርዓት መከበሩን እና የህዝብሰ ላምና ደህንነት መጠበቁን ማረጋገጥ፣

Ø  ህግ አስከባሪ አካላትን ዴሞክራሲያዊ አመለካከትና ሰብ-አዊ መብቶች ዙሪያ ግንዛቤ ማሳደግ፣

Ø  በክልሉውስጥእናአጎራባችክልሎችመካከልየሚነሱአለመግባባቶችንበሰላማዊመንገድመፍታት፣

Ø  የጸጥታ ተቋማትን አስተባብሮ መምራት እና ከሚመለከታቸው የፌደራል ተቋማት

ጋር በመተባበር የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ መሰረት አድርጎ የተቋቋመና የሚሰራ ቢሮ ነበር፡፡

በዚህም መሰረት በክልሉ ውስጥ ህግና ስርዓት ለማስከበር፣ የህዝቦችን ሰላምና ደህንነት

ለማረጋገጥና የጸጥታ ተቋማትን ድጋፍ በማጠናከር የተለያዩ አስራርሥ ርዓት በመዘርጋት

በክልሉ ውስጥ ስራዎች ሲሰሩ የቆዩ በመሆኑ የተቋሙ ዋና ተልዕኮው ሆኖ ቆይቷል፡፡

የክልሉን አስፈጻሚ አካላትን እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር176/2003 ዓ.ም

የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ የሚለውን የቀድሞውን ስያሜ እንደያዘ ከድሮው

በአዋጅ ቁጥር60/1994 ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት በተጨማሪ በትርፍ ላይ ያልተመሰረተ ዓላማ ይዘው

የተቋቋሙና በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ማህበራት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሀይማኖት ተቋማት

ህጋዊነት ከሚመለከተው አጋር አካላት ጋር በመተባበር እንዲሰራ፤ የህዝብ ግጭቶችን የመከላከል፣

የመፍታት እና የማስተዳደር ተግባር እና ኃላፊነት ተሰጥቶት ሲሰራ ቆይቷል፡፡

ስለሆነም የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ፣ ህግና ስርዓትን በማስከበር፣

የዜጎችን ሰብ-አዊና ዴሞክራሲያ ዊመብቶችን በማስከበር፣ በክልሉ ውስጥና

የአዋሳኝ ክልሎችን የህዝብ ግጭቶችን በመከላከልና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን የማጠናከር፣

ህገ-ወጥነትን በመከላከል፣ ተጠሪ ተቋማትን አስተባብሮ በመምራትና የተለያዩ ግብዓቶችን በማሟላት ከፌደራል

የፀጥታ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት በተደረጉ ጥረቶች ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

ክልሉን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማትና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ

በፀጥታ ስጋት ምክንያት እንዳይደናቀፍ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

የክልሉን አስፈጻሚ አካላት አዋጅ ቁጥር176/2003 ዓ.ም የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ

ትርፍ ላይ ያልተመሰረተ ዓላማ ይዘው የተቋቋሙና በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ማህበራት፣

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሀይማኖት ተቋማት ህጋዊነት ከሚመለከተው አጋር አካላት ጋር

በመተባበር እንዲሰራ በአዋጅ ቁጥር264/2011 ዓ.ም አንቀጽ36/2/ለ/ መሰረት በሰላምና

የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ ተፈፃሚነት አንደማይኖራቸው ተደንግጓል፡፡

በመሆኑም የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉ አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባራት

እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር264/2011 ዓ.ም ሰላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ

የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ተሰጥቶታት፡፡

I. በክልሉ ውስጥ ሰላምን ለማስጠበቅ ይሰራል፣ሕግና ስርአት መከበሩን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል

II.  አግባብ ካላቸው የክልልና የፌደራል መንግሥቱ አካላት ጋር በመተባበር በየትኛውም የክልሉ አካባቢ

የሚኖሩ ዜጎችና ማህበረ-ሰቦች ተገቢውን ሕጋዊ ጥበቃ እንዲያገኙ ያደርጋል፤

III.  የክልሉ ህዝብ ሰላም፣ ደህንነትና ነፃነት እንዲከበር የሚያስችሉ ስልቶችን ይነድፋል፤

IV. የሰላም እሴቶችን በመገንባትና በማስፋፋትረገድበህብረተ-ሰቡ ውስጥ ተከታታይነት

ያላቸው የግንዛቤና የንቅናቄ ተግባራት እንዲከናወኑ ያደርጋል፤

V. በክልሉ ውስጥ በሚኖሩ ግለሰቦች፣ ቡድኖችና ወይም የተለያየ ሀይማኖትም ሆነ እምነት ተከታዮች በሆኑ

ማህበረ-ሰቦች መካከል እርስ በርስ የመከባበርና የመቻቻል ባህል እንዲዳብር ለማድረግ

አግባብ ካላቸው የመንግሥት አካላት፣ እንዲሁም የባህልና የሃይማኖት ተቋማት ጋር በመተባበር ይሰራል፤

VI. ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስና በዝቡም ሆነ በመንግሥት ጥቅም ላይ በስውር ጉዳት

ለማድረስ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችንና ድርጅቶች ንበመከታተል ተግባራቸውን ቀድሞ ያመክናል፣

ተገቢውን ጥበቃ ያደርጋል፤

VII. በክልሉ ውስጥ በተዋቀሩ የበታች አስተዳደር እርከኖችም ሆነ ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሚነሱ

አለመግባባቶችና ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ሊፈቱ የሚችሉባቸውን ምቹ ሁኔታዎችይፈጥራል፤

VIII. ለአካባቢያዊ ግጭቶች መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በጥናት ይለያል፣

ህብረተ-ሰቡ ወደ ግጭትና አለመረጋጋት እንዳያመራ የቅድመ መከላከል እርምጃዎችን ይወስዳል፣

በሌሎች እንዲወሰዱ ያደርጋል፤

IX.በጥናት ላይ ተደግፎ የግጭት መንስኤዎች ንይለያል፣ ግጭት ሲከሰት ባህላዊና ዘመናዊ

የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም እንዲፈታ ይጥራል፣ በግጭቱ ውስጥ የተካፈሉ ተዋናዮችን

የማረጋጋት ናየማስተዳደር ተግባራትን ያከናውናል፤

ለሰላም በጋራ እንሰራለን የሚለው ሎጎ ትርጉም

ሰላም  ከብሄር፤ ከቋንቋ፤ ከማንነት፤ ከቀለምና ከዘር ጅረት የሚቀዳ  ሳይሆን በሁላችን  የእጅ መዳፍ ላይ  ያለችና በእያንዳንዱ ሰው አዕምሮ  ውስጥ የሚጠነሰስ  ሙሉ እምነትና ፍጹማዊ የፍቅር አተያይ ነው ፡፡ ሰላም ለእኔ፤ ለአንተ፤ ለእሱ፤ ለእሷ፤ ለእነሱ የሚያስፈልግ በመሆኑ እጅ ለእጅ ተያይዘን ከዚህ ደርሰናልናልና ወደፊትም የአብሮነታችንና የአንድነታችን  አምዕድ፤ የጥንካሬ ምንጭ፤ የአቃፊነት ስነ-ልቦና፤ የተፈጥሮ እኩልነት ገጸ- በረከት ነው ፡፡ ስለሆነም ሰላም በብዙ ማንነቶች ኡደት ውስጥ ፍቅርን መስጠትና መቀበል ማህበረሰባዊ እሴት ስለሆነች ለሁላችንም ታስፈልገናለችና በጋራ እንከባከባት፡፡