Web Content Display Web Content Display

Web Content Display Web Content Display

OFFICE HEAD AND VICE HEADS

Web Content Display Web Content Display

የልጅነት ጋብቻን ትኩረት ሰጥተን ልንከላከለው ይገባል፡፡

የአማራ ክልል ለሌላው ዓለም በመልካም ተሞክሮነት ሊወሰዱ የሚችሉ በርካታ ልንንከባከባቸውና ልናጐለብታቸው የሚገቡ ባህሎች፣ ልምዶችና እሴቶች ባለቤት የመሆኑን ያክል ሴቶችንና ህጻናትን ብሎም ማህበረሰቡን የሚጎዱ ነገርግን በተሳሳተ መንገድ እንደጠቃሚ ተወስድው የሚተገበሩ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚፈጸምበት ክልል ነው፡፡
ከእነዚህም ውስጥ ዋነኛው የልጅነት ጋብቻ ነው ፡፡ የልጅነት ጋብቻ በሀገራችንም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠውን አነስተኛ የጋብቻ እድሜ 18 ዓመት በመጣስ የሚፈጸም ጋብቻ በመሆኑ በመንግስትም ሆነ በአብዛኛው ማህበረሰብ ዘንድ የሚወገዝና የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ተግባር ነው፡፡
የልጅነት ጋብቻ የሴት ልጆችን የመማር መብት፣ ምኞችና ራዕይ እንዳይሳካ መሰናክል ከመሆኑም በላይ ለእነሱ የሚፈጠሩ መልካም ዕድሎችንም እንዳይጠቀሙ የሚያደርግ አሰከፊ ድርጊት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የስነተዋልዶ ጤና ችግሮች፣ የፍቺ፣ የመቀንጨር፣ የሴተኛ አዳሪነት፣ ስደት፣ እና ሌሎች አስከፊ ማህበረሰባዊ ጫናዎች ከማስከተሉም በላይ ለሀገር ድህነትና ለዜጎች ጉስቁልና ምክንያት ይሆናል፡፡
ስለሆነም ህብረተሰቡ እነዚህን ግለሰቦች በማጋለጥና መሰል ድርጊቶች ሊፈጸሙ ሲሉ ጥቆማ በመስጠት፤የሚመለከታቸው የህግ አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ግንዛቤ መፍጠሩ እንደተጠበቀ ሆኖ እነዚህ ግለሰቦች ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድባቸው በማድረግ፣ ለሴት ልጆች መልካም ህይወት የድርሻውን እንዲወጡ እንጠይቃለን፡፡
የብክመ ሴቶች ፣ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ