Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

ዜና ተፈጥሮ ሃብት

ያለፉት አመታት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራ ውጤት ዘንድሮ ሀዝቡ በነቂስ ለስራ እንዲሳተፍ አስችላል

በአማራ ክልል ጥር 1 ቀን በይፋ የተጀመረውና በሕዝብ ተሳትፎ የሚካሄደው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ በየአካባቤው ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በልማቱ እንዲሳተፍ ቀደም ባሉት አመታት የተሰራው የተ/ሀ/ል/ስራ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱ እና የልማቱ ውጤት ተቋዳሽ መሆን መቻላቸው ነው ሲሉ በደቡብ ጎንደር ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በልማቱ በመሳተፍ ላይ ያሉ አርሶ አደሮች ገለፁ፡፡ የክልሉ ግብርና ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሰሞኑን በደቡብ ጎንደር ዞን በደራ፣እስቲ እና አንዳቤት ወረዳዎች በመዘዋወር በተ/ሀ/ል/ስራ በመሳተፍ ላይ ያሉ አርሶ አደሮችን ባነጋገሩበት ወቅት ዘንድሮ በየአካባቢው በልማት ስራው የሚሳተፈው አርሶ አደር ቁጥር፤መጠን እና የሚሰሩበት ሰአት መጨመሩን ከአርሶአደሮች ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ለዚህም አርሶአደሮቹ በምክንያትነት ከጠቀሷቸው ውስጥ ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት ተ/ሀ/ል/ጥ የተሰራባቸው አካባቢዎች ከማገገማቸውም በተጨማሪ በታችኛው የተፋሰሱ አካባቢ ደርቀው የነበሩ ምንጮች መልሰው መፍለቃቸው፣የምንጮች ወንዞች ውሃ መጠን መጨመሩን አረጋግጠዋል፡፡ ከሰው እና ከእንስሳት ንክኪ በተከለሉ አካባቢዎች የበቀለውን ሳር ህ/ሰቡ አጭዶ በመውሰድ ለከብቶች ቀለብ ማዋል መቻሉ እና እንዲሁም በመሬት እጥረት ስራ አጥተው በችግር ላይ ነበሩ ልጆቻቸው ተደራጅተው በከብትና በንብ እርባታ ተጠቃሚ ለመሆን መቻላቸው በተፈጥሮ ሃብት ስራ ላይ ሙሉ አመኔታ እንዲያሳድሩ ከመቻሉም በላይ በስራው ላይ ለበለጠ ተሳትፎ እንዳነሳሳቸው ለህዝብ ግንኙነት ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ በስራ ላይ ቡድኑ አግኝቶ ያነጋገራቸው የዛራ ቀበሌ ነዋሪዋ ወ/ሮ ቃሊም ተገኘ እሳቸውም ሆነ አካባቢው ህ/ሰብ በፍላጎት በመስራት ላይ መሆናቸውን ከገለጹ በኋላ ቀደም ባሉ አመታት የተካሔዱ የልማት ስራዎችን አስመልክተው ከከብቶች ንክኪ አቁመናል፤አፈሩ ስለተረጋጋ የጣለው ዝናብ እዛው ሲሰርግ ነው የከረመው፤ደኖቹ አበቃቀላቸው ያስደስታል የበቀለውን ሳርም አጭደን ለከብቶቻችን ቀለብ አድርገናል፤አርሶአደሩ አምኖበት አሁን በደስታ ነው የሚሰራው በማለት ያለፉት አመታት ስራዎች ውጤት ለዘንድሮው ስንቅ እንደሆናቸው ለቡድኑ ገልጸዋል ፡፡

ሌላው የቀበሌ ነዋሪ አ/አደር ምስጋናው ጌትነት  ደግሞ ያለፉት አመታት የተካሄደው የልማት ስራ ውጤት ሲገልፁ ለልጆቻችን የምናወርሰው ሀብት መሬት ነው፡፡ መሬቱ ደግሞ ምርት ሊሰጥ የሚችል መሆን አለበት፡፡ ባለፈው አመት በሰራነው የተ/ሃ/ል/ስራ የመሬታችንን አፈር ጠብቀን አስቀርተናል፡፡ ለልማት የሚያስፈልገንን ውሃ በየቦታው ስንቆፍር ውሃ ማግኘት ችለናል፤ሰለሆነም ልጆቻችን በፈለጉት ላይ ቆፍረው ውሃ ማውጣት ይችላሉ፡፡ ከፈለጉት ላይ ማምረት ይችላሉ ደሰተኛ ይሆናሉ በማለት ያለፈው ስራ ተጨባጭ ለውጥ ማስገኘቱን ከገለፁ በኋላ እሳቸውም ሆኑ የአካባቢያቸው ኗሪዎቿ ዘንድሮ በልማቱ ላይ ያለውን ስሜት የገለፁት ፡፡

የደራ ወረዳ ዛራ ቀበሌ ግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ የኔማር በአካባቢያቸው ከ2003 ዓ/ም ጀምሮ የሚካሄደው የተ/ሀ/ል/ስራ ለህብረተሰቡ በአሁኑ ወቅት ሶስት የተቀናጁ ጥቅሞች አያስገኙለት በመሆናቸው ዘንድሮ ህዝቡ ለስራው ከፍተኛ ተነሳሽነት እንዳሳየ ገልፀዋል፡፡

የተቀናጁ ያሏቸውን ጥቅሞች ሲተነትኗቸው ደግሞ የአፈር ውሃ ጥበቃ ስራ የተካሄደባቸው ማሳዎች ላይ አ/አደሩ የተሻለ ምርት እያገኙ ነው፤ በማሳ ላይ በተሰራው እርከን ላይ ያለማው እፅዋት የእንስሳቱን መኖ ችግር ቀርፈውለታል፤የከርሰ ምድር ውሃም በቀላሉ ማግኘት እየተቻለ ነው ካሉ በኋላ እነዚህ ጥቅሞች ማጣጣሙ ሕ/ሰቡን ለልማት ስራው ለማስወጣት በዚህ አመት ምንም ችግር እንዳልገጠማቸው ገልፀዋል፡፡

ደቡብ ጎንደሮች በሰራችን ውጤታማ የመሆናችን ሚስጥር ስራን በአደረጃጀት መምራታቸው መሆኑን ገለፁ

በአዲሱ ሚሊኒየም በወረዳ ደረጃ የተዋቀረችው የደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ በአካባቢው የሚካሄደው የልማት ሰራ እና ውጤት በተለያዩ መድረኮች፣ በክልል አና በአገር አቀፍ ሚዲያ የወረዳዋ ስም በተደጋጋሚ እንዲነሳ አስችሏል፡፡

ወረዳዋም ከፌደራል መንግስት ጀምሮ በተዋረድ ባሉ አደረጃጀት ከፍተኛ ባለስልጣኖች የመጎብኘት ዕድል ስሟበሚዲያ በተደጋጋሚ ለመነሳት አና ከአጭር እድሜዋ የገዘፈ ዕውቅና እንድታገኝ ምክንያት እንደቤቶች በአረያነት ከሚጠቀሱት የልማት ሰራ ውስጥ አንዱና ምናልባትም ዋነኛው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ የሚሰጡት ትኩረት እና ያስገኙትና እያስገኘላቸው ያለው ጥቅም ነው ማለት ያስችላል፡፡

የግብርና ቢሮ የሕ/ግንኙነት የስራ ሂደት ቡድን ሰሞኑን በወረዳዋ ተዛውሮ ቀደም ሲል የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራ ተካሂዶባቸው ያገገሙ ወደ ቀድሞው ይዞታቸው በመመለስ ላይ የሚገኙ እና እንዲሁም ለአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ህይወት በመለወጥና በማሻሻል ረገድ የተገኙ ውጠየቶች  በወረዳዋ የልማት ሰራ በውጤታማነት ለሚካሄዱና ሕብረተሰቡንም ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያስቻላቸው ስራን በአደረጃጀት መምራት መቻሉ መሆኑን ቡድኑ በተ/ሃ/ል/ስራ ላይ ሲሳተፍ  ከተገኘው አርሶ አደሮችና አመራሮች ለመረዳት ችሏል፡፡