WELCOME  TO CIVIL SERVICE COMMSSON

 
ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተለያዩ የስራ ክፍል ዳሬክተሮችና ፈፃሚወች በካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
ታህሳስ 21/2013 ዓ/ም
*************************************************************
ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተለያዩ የስራ ክፍል ዳሬክተሮችና ፈፃሚወች በካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና ዙሪያ በኮሚሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ታህሳስ 20/2013 ዓ/ም የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የአብክመ አመራር አካዳሚ አማካሪና አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አለማ እና አቶ ታምሩ ተመስገን የካይዘን ስርአትን ለመተግበር ደግሞ የእውቀት፣ የክህሎትና የልምድ ችግር ሳይሆን የአፈፃፀም ችግር በመኖሩ ምክኒያት እንደሆነ እና ስልጠናው ይህን ክፍተት እንደሚሞላ ያላቸውን ተስፋ በመግለፅ ስልጠናውን መስጠት ብቻ ሳይሆን ውጤት እንዲመጣ ብሎም የመጣውን ለውጥ ለመገምገም የምያስችል ስርአት በመዘርጋት ክትትል እና ድጋፍ ይደረግ ብለዋል፡፡
በስልጠናው ተገኝተው ስልጠናውን የወሰዱት የኮሚሽኑ ሰልጣኞች በበኩላቸው ስልጠናውን አስመልክተው ሲናገሩ ካይዘንን በትክክል ለመተግበር ተከታታይ የሆን ስልጠና እና ፈቃደኛ የሰው ሀይል ዋነኛ መሳሪያዎች መሆናቸውን ገልፀው ስልጠናው ይህን ክፍተት እንደሚሞላ ያላቸውን ተስፋ በመግለፅ ስልጠናውን መውሰድ ብቻ ሳይሆን ውጤት እንዲመጣ ብሎም የመጣውን ለውጥ ለመገምገም የምያስችል የክትትል እና የድጋፍ ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ብለዋል።
የአብክመ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መሉቀን አየሁ በበኩላቸው የለውጥ ሥራዎችን በተደራጀ ሁኔታ ለማስኬድ መሰል የስልጠና ሥርዓት መዘርጋቱ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው በመጠቆም የአፈፃፀሙንም ውጤታማነት በተገቢው መንገድ ለመገምገም እንዲቻል በአደረጃጀቱ ላይ ጠንካራ ተግባራት ሊሠሩ እንደሚገባ እና የካይዘን አመራር ሥርዓት ለተሻለ ለውጥ፣ ጥራትና ምርታማነት የሚያነሳሳና ለተቋማዊ ለውጥ ድርሻው የጎላ ስለሆነ አመራሩንና ሠራተኛውን በማሳተፍ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባና አሳስበዋል።