Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

ቢሮው በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት የሚከተሉት ዝርዝር ተግባራት ያከናውናል

1.  በክልሉ ውስጥ የሚገኘውን የገጠር መሬት አይነትና መጠን አጥንቶና መዝግቦ ይይዛል፣ አስተዳደሩንና አጠቃቀሙን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣

2.  መሬቱ በተለያዩ ምክንያቶች ምርታማነቱን እንዳያጣና ከጥቅም ውጪ እንዳይሆን የመሬት ተጠቃሚዎች በይዞታቸው ላይ የተለያዩ እንክብካቤዎችን ማድረጋቸውን ይከታተላል፣ መሬታቸውን በግባቡ ለያዙት የተለያዩ የማትጊያ ዘዴዎችን ይቀይሳሉ ፣ ግዴታቸውን በማይወጡት ላይ ደግሞ እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡

3.  እንደሁኔታው ባህላዊና ዘመናዊ የቅየሳ ዘዴዎችን በመጠቀም እያንዳንዱን የመሬት ይዞታና ማስመዝገብ በምዝገባው መሠረት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተርና ካርታ ይሰጣል

4.  የመሬት ይዞታ መብት የተሰጣቸው ግለሰቦት /ድርጅቶች/ የይዞታ መብታቸውን እንደአግባብነቱ በውርስ፣ በኪራይ፣ በስጦታ ወይም በለውጥ የሚያስተላልፉበትን ስርዓት ያስፈጽማል፣ በመሬት ይዞታ ላይ የሚካሄዱ ለውጦችን በየጊዜው እየመዘገበ መረጃውን ወቅታዊ ያደርጋል፡፡

5.  የግል ባለሀብቶች በመሬት ላይ የልማት ስራ ከመጀመራቸው በፊት የአጠቃቀም እቅዳቸውን እየገመገመ  ያፀድቃል፣ የኢንቨስትመንት መሬት ሊዝ አስራርና  ተመኑን በየጊዜው እያጠና ለክልሉ መንግስት በቅርብ ያስወስናል፣ ከባለሀብቶች ጋር ውሎችን ይፈጽማል፣ በዕቅዳቸውና በውላቸው መሠረት ተግባራዊ በማያደርጉት ላይም በህግ አግባብ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡

6.  ለገጠር ቀበሌ ማዕከላትና አዳዲስ ለሚፈጠሩ አነስተኛ ከተሞች የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ በማዘጋጀት ይረዳል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡

7.  ለህዝብ ጥቅም ታልሞ በሚወሰድ እርምጃ ሲባል ከመሬታቸው የሚፈናቀሉ ባለይዞታዎች ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ እንዲያገኙና አማራጭ የኑሮ መሰረት እንዲኖራቸው ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል፣

8.  በዘመናዊ ሁኔታ በሚለሙ ትላልቅ የመስኖ ኘሮጀክቶች ውስጥ የሚኖሩ ቀደምት ባለይዞታዎች በሕግ አግባብ የመሬት ሽግሽግ በማካሄድ የሁለተኛ ደረጃ ደብተርና ካርታ እንዲያገኙ ያደርጋል፣

9.  በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ አስተዳደራዊ እርከኖች፣ ይዞታዎችና ማሣዎች ልዮ ኮድ ይሰጣል፣ የተሰጠውን መለያ ኮድ ሌሎች መ/ቤትና የልማት ተቋማት እንዲገለገሉበት ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣

10.የክልሉን የአካባቢ ጥበቃ፣ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም በሚመለከቱ ጉዳዮች አግባብ ላላቸው አካላት ስልጠና፣ ምክርና ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፣

11.የብዝሀ ሕይወት የስርዓት ምህዳሮችንና የሌሎች የአካባቢ ሀብቶችን አያያዝ አጠቃቀምና ልማት ለማሻሻል የሚያግዙ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ በጥናቱ ውጤት መሰረት ለተለዮ ችግሮች የአጭርና የረጅም ጊዜ የመፍትሄ እርምጃዎችን ይወስዳል፣

12.የአካባቢ ሀብቶችን አስመልክቶ የዋጋ ትመና ጥናቶችን ያካሂዳል፣ በትመናው ውጤት መሰረት ኘሮግራሞችና ኘሮጀክቶች ሲነደፉ በአጭጭነት ስሌታቸው ውስጥ የአካባቢ ሀብቶች ዋጋ እንዲካተት ያደርጋል፣ በትግበራ ወቅት ለሚደርሰው ማናቸውም የአካባቢ ሀብት ጥፋት በሀብት ትመናው መሰረት ተመጣጣኝ ካሣ እንዲከፈል ያደርጋል፣

13.የአካባቢ ደህንነትን ለማስከበር ስልጣን፣ ኃላፊነትና ተግባር በተሰጣቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ባልሆኑ ተቋማት ተግባር ላይ የምርመራ የክትትል ሥራዎችን ያከናውናል፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡት ላይ ደግሞ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣

14.የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማዎችን ለማካሄድ የሚያስችሉ ስልቶችን ይቀይሣል፣ ሪፖርቶችን በመመርመር የእርምትና የማስተካከያ አስተያየቶችን ይሰጣል፣ ተስተካክለው በቀረቡ ሰነዶች አንፃር የይሁንታ ፈቃድ ይሰጣል፣

15.በከተማ አስተዳደር ክልል ውስጥ የጠቃለሉ የገጠር ቀበሌዎችን መሬት ነክ አስተዳደርና አጠቃቀም ይወስናል፣ ይመዘግባል፣ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተርና ካርታ ይሰጣል፣