Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

የቆሻሻ አወጋገድ በጎንደር ከተማ

 

መግቢያ


በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን ዋና ከተማ ጎንደር በ16ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ፋሲለደስ ዘመነ መንግስት የተቆረቆረች ለመሆኗ መረጃዎች ይጠቅሳሉ፡፡ የጎንደር ከተማ ለብዙ ዘመናት የኢትዮጵያ ርእሰ ከተማ በመሆንም አገልግላለች፡፡ በከተማዋ ከብዙ ዓመታት በፊት የተቆረቆሩ አብያተ ክርስቲያናትና በዘመኑ የነበሩ መሪዎች ያስገነቡአቸው እንደ ፋሲለደስ ቤተመንግሥትና ሌሎችም ቅርሶች ይገኙባታል፡፡ እንደ ዊኪፒዲያ መረጃ የጎንደር ከተማ የቆዳ ስፋት 40.27 ኪ/ስኴር ካሬ ነው፡፡ ከጎንደር ከተማ የከተማ ፕላን፣ ጽዳትና ውበት ዋና የሥራ ሂደት ባለሙያዎች በተገኘው መረጃ ከተማዋ 12 የከተማ፣ 1 የሳተላይት እና 11 የገጠር ቀበሌ አስተዳደሮችን ይዛለች፡፡/read more/dry wast gonder city