በአማራ ክልል 4ቱ ሜትሮፖሊታን ከተሞች

 

የቆሻሻ አያያዝ ስርዓት

መግቢያ


ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴና ኮምቦልቻ በአማራ ክልል ውስጥ በሜትሮፖሊታን ደረጃ የተቋቋሙ ከተሞች ናቸው፡፡ እነዚህ ከተሞች በሕዝብ ብዛት፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በተለያዩ መሰረተ ልማቶች  መስፋፋት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ከተሞች ናቸው፡፡ በየከተሞቹ ያለው የልማት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመሄዱ ልዩ ትኩረት እንዲሰጣቸው አድርጓል፡፡ ከተሞቹ በልማት ከማደጋቸው ጋር ተያይዞ ለተለያዩ የአካባቢ ችግሮች መጋለጣቸው አልቀረም፡፡ ከሚጠቀሱት ዋና ዋና ችግሮች አንዱ ደግሞ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ብክለት ነው፡፡ በዚህ ጽሁፍ በየአንዳንዱ ከተማ ያለውን ችግር በመጠኑም ቢሆን በቅደም ተከተል እናያለን፡፡ /read more/

 

 

ርዕሰ አንቀፅ

አካባቢና ልማት ተነጣጥለው ሊታዩ አይገባም!

 

        ከድህነት የተላቀቀችና መካከለኛ ገቢ ያላት ኢትዮጽያ እውን ከማድረግ አኳያ በሀገራችን ብሎም በክልላችን ከሚከናወኑ ፈርጀ ብዙ ተግባራ መካከል የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅና መንከባከብ ፣የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርአት ግንባታን ማጠናከር ጉልህ ስፍራ በያዘበት ወቅት ላይ እንገኛለን ።በመሆኑም አካባቢ ጥበቃና ልማት ተጣጥመው እንዲሄዱ በርካታ ስራዎች መስራት ያስፈልጋል።/read more/metshet 2004 akababina limat/