Web Content Display Web Content Display

መግቢያ

የክልል መስተዳድር ም/ቤት ማለት በ1994 ዓ.ም ተሻሽሎ በወጣው የአማራ ብሔራዊ ክልል ሕገ-መንግስት አንቀጽ 57 ንኡስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው የብሔራዊ ክልላዊ መንግስቱ ከፍተኛ አስፈፃሚ አካል ነው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በብሔራዊ ክልላዊ መንግስቱ ከፍተኛ የአስፈፃሚነት ስልጣን የተሰጠው አካል እንደመሆኑ መጠን ተሻሽሎ በወጣው የ1994 ዓ.ም የክልሉ ሕገ-መንግስት አንቀጽ  58 ድንጋጌዎች ስር የተጣለበትን ባለብዙ ፈርጅ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት የቅድሚያ መወያያ አጀንዳዎችን እየቀረፀና በአባላቱ እያስፀደቀ በየጊዜው መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባዎችን በማካሄድ በክልሉ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ጉዳዬች ዙሪያ በንቃት መምከር፣መከራከርና ውሳኔዎችን ማሳለፍ የሚጠበቅበት በመሆኑ፤ ለዚህም ይረዳው ዘንድ ምክር ቤቱ በሚገባ ተደራጅቶ መደበኛ ስብሰባዎች የሚካሄድባቸውን ጊዜያት፣ስብሰባው የሚመራበትን፣ውይይቶች የሚደረጉበትንና ውሳኔዎች የሚተላለፋበትን ውስጣዊ የአሰራር ስነ-ስርዓት መወሰኛ ደንብ አውጥቶ ስራ ላይ አውሏል፡፡