Web Content Display Web Content Display

መመሪያ ቁጥር 22/2007 ዓ/ም

መደበኛ ነዋሪነታቸው በውጭ አገር የሆነና በአማራ ብሔራዊ ክልል ከተሞች ውስጥ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ኢትዩጲያውያንና የሌላ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ-ኢትዩጲያዊያን የሚመዘገቡበትንና የሚስተናገዱበትን የአሰራር ስርዓት ለመወሰን የወጣ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት መመሪያ

መመሪያ ቁጥር 22/2007 ዓ/ም መደበኛ ነዋሪነታቸው በውጭ አገር የሆነና በአማራ ብሔራዊ ክልል ከተሞች ውስጥ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ኢትዩጲያውያንና የሌላ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ-ኢትዩጲያዊያን የሚመዘገቡበትንና የሚስተናገዱበትን የአሰራር ስርዓት ለመወሰን የወጣ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት መመሪያ የኢፌዴሪ መንግስት በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን በትውልድ አገራቸው ሁሉን አቀፍ የልማት እንቅስቃሴ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያስችል የዲያስፖራ ፖሊሲ ቀርፆ ከታህሣሥ ወር 2005 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኝ በመሆኑ፤ በሰነዱ ክፍል ሁለት ቁጥር /5/ ንዑስ ቁጥሮች /1/ እና /4/ ስር እንደሰፈረው ከዚሁ ፖሊሲ ግንባር ቀደም ግቦች መካከል "በውጭ የሚኖሩ ኢትዩጲያውያንን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ" እና "የውጭ ምንዛሪ ማስገቢያ መንገዶችንና የዲያስፖራውን ተሳትፎ ማሳደግ" የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ሆነው በመገኘታቸው፤ ዲያስፖራው በግልና በማህበር ተደራጅቶ በክልሉ ከተሞች ውስጥ ቁጠባን መሠረት ያደረገ የመኖሪያ ቤት መገንቢያ ቦታ ስለሚያገኝበት ሁኔታ በጥናት ላይ የተመሠረተ የአሠራር ስርዓት እንደሚዘረጋ በሀገሪቱ የቤት አቅርቦት ስትራቴጅ ማዕቀፍ ውስጥ ጭምር የተካተተ በመሆኑ፤ download for more