Web Content Display
የጽ/ቤቱ ተልዕኮ
ለመስተዳድር ም/ቤቱ ደረጃውን የጠበቀና ህገ መንግስታዊ ሀላፊነቱን በብቃት መወጣት የሚያችለውን ሁለገብ ድጋፍ በመስጠትና የአገልግሎት አሰጣጡን ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለውና ወጤታማናቱ በተረጋገጠ መንገድ በማከናወን፤ የበላይ አመራሩ ከሚያስተባብራቸው ክልል አቀፍ አስፈጻሚ መስሪያቤችና በተዋረደ ከሚቆጣጠራቸው የየእርከኑ አስተዳደር አካላት ጋር ያሉት ግንኙነቶች እንዲሳለጡ፤ በህግ የበላይነት አስተሳሰብ ላይ ተመስርተው እንዲፈጸሙ በበላይና በበታች የመንግስት አካላት መካከል ግልጽ የሆነና ተጠያቂነት ያለበት አሰራር እርአት ማስፈን።
የጽ/ቤቱ ራዕይ
d አማራጭ 1
የመስተዳድር ም/ቤቱ በአገልግሎት አሰጣጣችን እረክቶ በክልሉ ተግባራዊ እንዲሆኑ የሚያወጣቸው ህጎች የክልሉን የኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፓለቲካዊ ችግሮችን በ2022 ዓ.ም ተፈተው ሰላም ደሞክራዊና ልማት የሰፈነበት ክልል ተፈጥሮ ማየት
d አማራጭ 2
የመስተዳድር ም/ቤቱንም ሆነ ሌሎች አገልግሎት የሚያገኙ አካላት በ2022 ዓ.ም ረክተው ማየት
d አማራጭ 3
በ2022 ዓ.ም ሁለንተናዊ ገጽታው የተገነባ ሁሉም አካል በአገልግሎት አሰጣጡ የሚረካበት ተቋም ሆኖ ማየት
የጽ/ቤቱ እሴቶችና የሥራ መርሆዎች
ጽ/ቤቱ የሚያቅዳቸውን እቅዶች በተሟላ መልኩ ለመፈፀም የሚከተላቸው የሥራ መርሆዎችና እሴቶች የሚከተሉት ናቸው፦
ð በየደረጃው ብቃት ያለው አመራር እንዲፈጠር የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን አንቀጥላለን፣
ð ህዝባዊ ወገንተኝነታችንን በስራ እናረጋግጣለን፣
ð ፍትሃዊ የሆነ ህግ እንዲወጣና ተግባራዊ እንዲሆን እንሠራለን፣
ð የህግ የበላይነትን እናከብራለን፣
ð የባለጉዳዮቻችንን ጥያቄ በጥሞናና በትህትና እናዳምጣለን፣ በወቅቱ ተገቢውን ምላሽ እንሰጣለን፣
ð በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የሥርዓተ ጾታ መርህን እንከተላለን፣
ð የሕብረተሰቡንና የመ/ቤቱን ሠራተኞች ዲሞክራሲያዊተሣትፎ ያረጋገጠ የአሰራር ስርአት እንከተላለን፣
ð የግለሰቦችን ጥረትና ተነሳሽነት እንዲጎለብት ጠንክረን እንሠራለን፣
ð ተደጋግፎ የመስራት ባህልና መተማመን በመ/ቤቱ ውስጥ እንዲሰፍን እናደርጋለን።
ð የግለሰብና የቡድን መብትን እናከብራለን፣