Web Content Display
የጽ/ቤቱ አመሰራረት
የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር 185/2003 ዓ.ም መሰረትመቀመጫው በክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር ሆኖ በስምንት ዳሬክቶሬቶች፣በ5የስራቡድኖች እና 164 የሰው ሀይል ይዞ የተደራጀ ነበር፡፡ይሁን እንጅ ጽ/ቤቱ የአደረጃጀት ማሻሻል በማስፈለጉ በማሻሻያ ደንብ ቁጥር 179/2011 መሰረት በአዲስ አደረጃጀት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡በተዋረድም በዞን ከተማአስተዳደሮችን ጨምሮ 15 ጽ/ቤት፣ በወረዳ ደረጃ 143 ጽ/ቤቱች፣56 የከተማአስተዳድር ከንቲባ ጽ/ቤቶች እና በ 3968 ቀበሌዎች መዋቅሩን በመዘርጋት ለክልሉ ህዝብ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ተቋምነው፡