Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

የኢንቨስትመንት አማራጮች

    1.የክልሉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴና ምቹ ሁኔታዎች

    የሀገራችንን የኢኮኖሚ ልማት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ህዝቦች ካሉበት የድህነት አረንቋ ተላቀው የተሻለ ህይወት እንዲመሩና የኑሮ ደረጀቸውን  ከፍ እንዲል ለማስቻል ልዩ ትኩረት ከሚሰጣቸው ቁልፍ የልማት አጀንዳዎች መካከል ኢንቨስትመንትን ማበረታታትና ማስፋፋት በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡

    ይህንኑ ቁልፍ የልማት አጀንዳ ስኬታማ ለማድረግ ደግሞ የልማቱ ሞተር የሆነውን የአገር ውስጥ እና የውጪ ልማታዊ ባለሃብት አቅሙ እንዲጐለብትና ተወዳዳሪና ትርፋማ እንዲሆን በሚያስችል የኢኮኖሚ ፖሊሲና ስትራቴጅ መደገፍ በማስፈለጉ መንግስት ኢንቨስትመንቱን ለማበረታታት፣ለማስፋፋትና ለማስተግበር በ1984 ዓ/ም በአገር አቀፍ ደረጃ የኢንቨስትመንት አዋጅ በማውጣትና ወደ ተግባራዊ  እንቅስቃሴ በመገባቱ በክልላችን በርካታ ኘሮጀክቶችን በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ማሰማራት በመቻሉ ኢኮኖሚውን ከመደገፍ በላይ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡  ይህም ህዝቡ በየደረጃው የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ያስቻለ በጐ የኢንቨስትመንት ድምር መኖሩን የሚያመለክት ጉዳይ ነው፡፡

    ኢንቨስትመንቱን በዘላቂነት ለማበረታታትና ለኢኮኖሚው የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በአግባቡ እንዲወጣ ለማስቻል መንግስት የኢንቨስትመንት አዋጆችን በተለያየ ጊዜ በመፈተሽና ማሻሸያ በማድረግ ዘርñ በተሻለ የሚደገፍበትን አሠራር ተግባራዊ ማድረግ በመቻሉ በክልሉ ያሉ የኢንቨስትመንት ኘሮጀክት፣ የተመዘገበ ካፒታልና የሥራ ዕድል ፈጠራ በአብዛኛው ከጊዜ ወደ ጊዜ  ዕድገት እንዲያሳዩ የበኩሉን ሚና  ተወጧል፡፡

    ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ

Document Library Display Document Library Display

Minimize Maximize