Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማቋቋምና ስልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 176/2003 ዓ.ም መሠረት የአብክመ ፍትህ ቢሮ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል፡፡

 1.   የክልሉ ፍትህ ሥርዓት የሚሻሻልበትን ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፤

2.   የሕግ ጉዳዮችን በሚመለከት የክልሉን መንግሥትና ተቋማቱን ያማክራል፤

3.   የክልሉ ሕብረተሰብ መብትና ግዴታውን አውቆ ሕግ አክባሪና አስከባሪ እንዲሆን በተለያዩ     

       ዘዴዎች የንቃተ ሕግ ትምህርት ይሰጣል፤

4.   ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አካላት ጥያቄ ሲያቀርቡለት በክልሉ መንግሥት የሚወጡ ሕጐችና  

      ደንቦችን ያረቃል፤

5.   የክልሉን መንግሥት ሕጐች፤ የኮዲፊኬሽንና የማጠቃለል ሥራዎች ያከናውናል፣

6.   የየደረጃውን ዓቃብያነ ሕግ በበላይነት ይመራል፣ ይቆጣጠራል፤

7.   በሕግ መሠረት በድርድርና በእርቅ እልባት ማግኘት የሚችሉ የወንጀል ጉዳዮችን አይቶ 

      ይወስናል፤

8.   የእጅ ተፍንጅ ወንጀሎች በተፋጠነ ሥነ-ሥርዓት ውሣኔ የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቻል፤

      ለዚህም ከፖሊስና ከሌሎች ጉዳዩ  ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ ይሠራል፤

9.   በማረሚያ ቤት፣ በማረፊያ ቤት፣ በጠባይ ማረሚያና በጊዜያዊ የእስረኞች መጠለያ የሚገኙ 

      ሰዎች  በአግባቡ መያዛቸውንና ሕጋዊ መብታቸው መከበሩን ያረጋግጣል፤

10.  በክልሉ መንግሥት ፍ/ቤቶች ስልጣን ሥር የሚወድቅ ወንጀል ተፈጽሟል ብሎ ሲያምን

        ምርመራ እንዲደረግ ያዛል፣ በቂ ምክንያት ሲኖረው የተጀመረ ምርመራ እንዲቆም ወይም  

        ተጨማሪ ምርመራ እንዲከናወን መመሪያ ይሰጣል፣ በሕግ መሠረት   የወንጀል ክስ  

         ይመሠርታል፣ያነሣል፤

11.  ለወንጀል ጉዳይ ምስክሮች በወቅቱ መጥሪያ እንዲያደርስና ምስክሮችንም ወደ ፍርድ ቤት  

        እንዲያቀርብ ለፖሊስ ትዕዛዝ  ይሰጣል፤

12.  አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የዓቃቤ ህግ ምስክሮች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያገኙ ያደርጋል፤

13.  በወንጀል ድርጊት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውንና ገንዘብ ከፍለው መከራከር የማይችሉ ወይም

       አቅም የሌላቸውን ሰለባዎች፣ የአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ድሀ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣

        ህፃናት ወይም የኤች.አይቪ./ኤድስ ሕሙማንን ወክሎ በድርድር ወይም በክልሉ ፍ/ቤቶችና

        በሌሎች የዳኝነት አካላት ዘንድ ክስ በመመስረትና በመከራከር እነዚሁ ወገኖች ካሣ እንዲያገኙና

        ፍትሃብሔር ነክ ጥቅማቸው እንዲከበር ያደርጋል፤

14.  የክልሉን መንግሥትና ሕዝብ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ይቻል ዘንድ በልዩ የሥራ ጠባያቸው

        ምክንያት የራሣቸው ነገረፈጅ ካላቸው መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ውጭ ያሉትን  

         ክልላዊ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በመወከል በፌዴራልና በክልል  ፍ/ቤቶች፣ በማናቸውም  

          የዳኝነት ሰሚ አካል ወይም የሽምግልና ጉባዔ ክስ ይመሠርታል፣ ይከራከራል፤

15.  በልዩ ሁኔታ የራሣቸው ነገረፈጅ ያላቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች  

        ተከራካሪ በሚሆኑባቸው የፍትሐብሔር ክሶችና የመብት ጥያቄዎች ላይ የህግ ድጋፍ ሲጠይቁ 

         እገዛ ያደርጋል፤

16.  በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የክልሉ መንግሥት መስሪያ ቤቶች መካከል የሚነሱ

       ፍትሐብሔር ነክ የመብት ጥያቄዎችን በማደራደር የመጨረሻ እልባት እንዲያገኙ ያደርጋል፤

17.  በሕግ ከሚወሰነው የገንዘብ መጠን በላይ የሕብረት ሥራ ማሕበራትን በመወከል ክስ

       ይመሠርታል፣ ይከራከራል፣ እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎች የሕግ ድጋፎችን ይሰጣል፣

18.  ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ድሀ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ፍትሕ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ  

       ጠበቆችንና የጠበቆችን ማህበራት፣ ልዩ   የጥብቅና ፈቃድ ያላቸውን የሲቪክ ማህበራት

       በማስተባበር ነፃ የሕግ ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤

19.  በክልሉ መንግሥት ፍ/ቤቶች መከራከር ለሚችሉ ጠበቆች ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሣል፣ 

         ይቆጣጠራል፣ ይሰርዛል፤

20.  በክልሉ ውስጥ የሰነዶችን ሕጋዊነት ያረጋግጣል፣ ይመዘግባል፡፡