Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

በፍትሐብሔር ጉዳይ የክልሉን መንግሥትና ህዝብ መብትና ጥቅም ማሥጠበቅ ዋና የሥራ ሂደት

  1. በሥራ ሂደቱ የሚሠጡና የማይሰጡ አገልግሎቶች

   1.1. በፍትሐብሔር የሥራ ሂደት የሚሠጡ አገልግሎቶች፣

  • በመንግሥት መ/ቤቶች የሚቀርቡ የውል ረቂቅ ወይም ምርመራ የውል ሰነድ ዝግጅት እና የህግ ምክር ጥያቄዎችን በየደረጃው መርምሮ በተቀመጠው የጥራት፣ የጊዜ እና የውጭ ስታንዳርድ መሰረት አሥተያየት መስጠት ወይም የውል ሰነድ ማዘጋጀት፣
  • የመ/ቤቶችን ባህሪ በማጥናት የሚያሥፈልጓቸውን የውል ረቂቆችና የሥራ መመሪያዎችን አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ማዋል፣
  •  በመ/ቤቶች ለመንግሥትና ህዝብ ገንዘብ ብክነት /ምዝበራ በር የሚከፍቱ አሠራሮችን በማጥናት ክፍተቶችን የመዝጋትና አሥቀድሞ የመከላከል ሥራ መሥራት
  • በመ/ቤቶች የሚቀርቡ የክሥ ወይም የመልስ ይቅረብልኝ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ ለመሥጠት ያመች ዘንድ በቂ ማሥረጃዎችን ተንቀሣቅሶ የማሰባሰብ፣ንብረት የማጣራት ሥራዎችን የመሥራት፣
  • አለመግባባት /ክርክር/ የተነሣበትን ጉዳይ አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴን በመጠቀም በድርድር የመፍታት፣
  • ከክስ በፊት ወይም በኋላ በሥራ ሂደቱ የእግድ ትእዛዞችን በማስተላለፍ ተከሣሾች ንብረት እንዳያሸሹ /እንዳያባክኑ/ማድረግ፣
  • አለመግባባቶችን /ክርክሮችን/በድርድር መፍታት ካልተቻለ አሥቀድሞ የተሠበሰበውን ማሥረጃ መሰረት በማድረግ ጥራት ያለው ክሥ/መልስ/ ማዘጋጀትና መ/ቤቶችን ወክሎ የመከራከር፣
  • ክርከር በተነሣበት ጉዳይ በፍ/ቤት ክስ ማቅረብ አዋጭነት የሌለው በሆነ ጊዜ የክስ አይቀርብም ውሣኔ መሥጠት፣
  • ክስ ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት በማቅረብ በቀጠሮ መሰረት ቅድመ ዝግጅት አድርጐ በመገኘት ብቃት ያለው ክርከር ማካሔድ፣
  •  ፍ/ቤቶች የሚሠጧቸው ትዕዛዞች ፣ብይኖችና ውሣኔዎች የመንግሥትና ህዝብን መብትና ጥቅም ያስጠበቁ መሆኑን የማረጋገጥና ያላስጠበቁ ከሆነ በየደረጃው ይግባኝ /ሰበር/በማቅረብና በመከራከር ውሣኔውን ወይም ብይኑና ትዕዛዙ እንዲሥተካከል ማድረግ፣
  •  በድርድር ወይም በፍ/ቤት ውሣኔ ያገኙ ጉዳዮችን ለአፈፃፀም ሲባል ድጋሜ ወደ ፍ/ቤት መወሰድ ሣያሥፈልግ በሥራ ሂደቱ ማሥፈፀም፣
  •   ውሣኔውን በማሰፈፀም ረገድ ንብረት የማሥገመት፣ጨረታ የማሥፈፀም
  •  ልዩ ልዩ የማሥረጃ አሰባሰብና አጠባበቅ ዘዴዎችን ሥራ ላይ ማዋል፣
  •  ለተከሣሾችና ለምሥክሮች መጥሪያና ትዕዛዝ እንዲደርሥ ማድረግ፣
  • በሥራ ሂደቱና በፍ/ቤት የሚሠጡ ትዕዛዞችን የማሥፈፀም፣
  • የወንጀል ሰለባ የሆኑ ድሃ ወገኖችን በመወከል ያጡትን ጥቅም የማስከበርና ካሣ እንዲያገኙ የማድረግ፣
  • አቅመ ደካማ ተብለው ከተለዩት መካከል ሆነው በተጨማሪ ድሃ መሆናቸው ከሚመለከተው አካል ማሥረጃ የሚያመጡ እንደሴቶች፣አካል ጉዳተኞች አረጋውያን፣የኤች አይቪ ኤድሥ ህሙማን መብትና ጥቅም ለማሥከበር የሚሰጠው አገልግሎት በጠበቆች፣ በጠበቆች ማህበርና ፍ/ቤት ለመቆም ልዩ የጥብቅና ፈቃድ በሚሰጣቸው ሲቪክ ማህበራት ሲሰራ አገልግሎቱን የመምራት የመከታተልና የመቆጣጠር ሥራ መሥራት አሥፈላጊም ሲሆን በራሱ የመሥራት፣
  •  ከህፃናት ጋር በተያያዘ ያለዕድሜ ጋብቻና የሞግዚት/አሣዳሪ/ አያየዝ እንዲሁም ሌሎች ከህፃናት መብት ጋር ተያያዥ የሆኑ የመብት ጥሰቶችን ለመከላከል የሚሠጠውን አገልግሎት ድሃ መሆን አለመሆናቸውን ከግምት ውስጥ ሣይገባ በሥራ ሂደቱ አገልግሎቱን የመሥጠት፣
  • በማህበራዊ ፍ/ቤት የሚሠጡ የድህነት ማሥረጃዎችን ታማኝነት ለማረጋገጥ የአሠራር ግንኙነት የመፍጠርና የማመቻቸት ሥራ መሥራት፣
  • የህብረት ሥራ ማህበራትን ህልውና በሚነካ መልኩ የሚፈጠሩ የገንዘብ /የንብረት ጉድለትና ብክነቶችን/ ተከታትሎ መብትና ጥቅማቸውን የማሥጠበቅ ሥራ መሥራት የሚሉት ናቸው፡፡

Pages: 1  2  3  4