Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳደር ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ   ሞገስ ደምሴ  የተባለው ግለሰብ በእስራት ሊቀጣ የቻለው  በከተማው   በመንሳቀስ መጋቢት ወር 2006 ዓ/ም የስርቆት ስልቱን በመቀየስ በገበያ ቦታ በመዘዋወር ጥሩ የሚባሉና ዘመናዊ ሞባይል ይዘው ያያቸውን ግለሰቦች እየተከታተለ የሚገቡበትን ቤት ካየ በኋላ ተከሳሹ ሞባይል ይዘው ከገቡበት አከባቢ ያለን የከብት ቀለብ ገለባ  እና የሳር ክዳን ቤት በማቃጠል ህ/ሰቡ ቃጠሎን ለማጥፋት ወደ ተቃጠለበት ቦታ ሲሄድ ህፃን ልጅ በመላክ በቤታቸው ቃጠሎውን ለማጥፋት ሲንቀሳቀሱ ወደ ቤታቸው በመግባት ቀን የተመለከታቸውን ሞባይሎችና ከቤት ውስጥ ያገኘውን ገንዘብ በመስረቅ ይሰወራል፡፡

 በተደጋጋሚ የዚህ አይነት ወንጀሎች በመፈጸማቸው የከተማው ፖሊስም የክትትል አድማሱን በማስፋት ወንጀል ፈጻሚውን በመለየት በህግ ቁጥጥር ስር ሲያውለው  ተከሳሹ 6 የተለያዩ ሳምሰንግ   ሞባይልና  ከተለያዩ ግለሰቦች የሰረቃቸውን ንብረቶች ከተከሳሹ እጅ ሊይዝ መቻሉን ፖሊስ ገልጻል፡፡

የቆቦ ከተማ ፖሊስ ምርመራውን  በሰው ማስረጃ በማጠናከር ለሚመለከተው የፍትህ አካል ልኳል፡፡  የምርመራ መዝገብ የደረሰው የራያ ቆቦ ወረዳ ፍ/ቤት ጉዳዩን ሲያጣራና ሲመረምር ከቆየ በኋላ ተከሳሽ ሞገስ ደምሌ  ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ጥቅምት 21/2007 ዓ/ም በቆቦ ከተማ ባስቻለው መደበኛ ችሎት የ17 ዓመት ፅኑ እስራት የተወሰነበት መሆኑን የወረዳው ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት ኢ/ር ዳዊት ዝናቤ ገልፀዋል ሲል ሪፖርተራችን ዝናቤ በላይ ዘግቧል፡፡

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

በቅናት በመነሳሳት ፍቅረኛዉን የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በኢ/ር መንገሻ አውራሪስ

 

 በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳደር ሚያዚያ 3 ቀን 2006 ዓ/ም የቆቦ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነችውን ወርቅውሃ አሊ የዕለቱን የትምህርት ገበታዋን ለመከታተል ወደ ት/ቤቷ ታመራለች፡፡ ያቺ ቀን ግን ለእሷ የመጨረሻዋ ቀን ነበረች፡፡ የእረፍት ጊዜዋን ለመጠቀም ከት/ቤት ግቢ ውስጥ በመዘዋው ላይ እንዳለች  የፍቅር ጓደኛዋ የነበረው ወጣት ዩሐንስ አዳነ በተሣሣተ ግንዛቤ በቀጥታ መንፈስ በመነሳሳት የትምህርት ቤቱን አጥር ዘሎ በመግባት   ወጣቷን ተማሪ አንገቷ ላይ በጩቤ በመውጋት ከአከባቢው ሊሰውር ሲሞክር በህብረተሰቡ ትብብር ሊያዝ ችሏል፡፡

የቆቦ ከተማ አስተዳዳር ፖሊስ ምርመራውን በማጣራት ለሰ/ወሎ ዞን ፍትህ መምሪያ ልኳል፡፡ የዞኑ ፍትህ መምሪያው የምርመራ መዝገቡን ተመልክቶ ለሰ/ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/በት በላከው መሰረት የተከሳሹን ጥፋተኛነት የተመለከተው የሰሜን ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት  ጥቅምት 18 ቀን 2007 ዓ/ም በዋለው ችሎት በተከሳሽ ዩሐንስ አዳነ ላይ የ18 ዓመት ፅኑ እስራት የወሰነበት መሆኑን የከፍ/ፍ/ቤት ህዝብ ግንኙነት መኮነን መለሰ ገልፀዋል፡፡

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

በተከሳሽ እና ምስክር አቀራርብ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ፡፡

በኢ/ር መንገሻ አውራሪስ

በሰሜን ጐንደር ዞን  ከሚገኙ ወረዳዎች እና ከጐንደር ከተማ አስተዳዳር የተውጣጡ የወንጀል ምርመራ ባለሙያዎች፣ የአቃቢ-ህግ ባለሙያዎች እና የተከሳሽ ምስክር አቀራርብ ሠራተኞች በተገኙበት የ3 ቀን ስለጠና ተሰጥቷል፡፡

በምርመራ ጥራት የሚታዩ ችግሮችን የፖሊስ፣ የዐ-ህግ እና የፍ/ቤት ሠራተኞች ተቀናጅተው በመስራት የህብረተሰቡን የፍትህ እጦት ችግር ለመቅረፍ የተቀላጠፈ አሰራር ለመስራት የሚያስችል መሆኑን በውይይቱ ላይ የተገኙት አመራሮት ተናግረዋል፡፡

በተለይም ተከሳሽና ምስክር ባለማቅረብ በምርመራ ጥራት መጓደል እና ቋሚ አድራሻ ሳይኖራቸው በትራፊክ አደጋ ፤በዘረፋና ቅሚያ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ግለሰቦች በዋስ መብታቸው ከወጡ በኋላ በጊዜ ቀጠሮአቸው ባለመቅረባቸው በርካታ መዝገቦች ይዘጋሉ፡፡ በዚህም ተጠርጣሪ ግለሰቦች ፍትህ ሣያገኙ ሲቀሩ ህብረተሰቡ በፍትህ ስርዓቱ ላይ አመኔታ እንዲያጣ እያደረገው መሆኑን ተሳታፊወቹ ተናግረዋል፡፡

የፍትህ አካላት ከፍተኛ አመራሮቹ በበኩላቸው የሚዘጉ መዝገቦችን ለማስቀረት ህገ-መንግስቱና ህግን መሰረት በማድረግ ተቀናጅተን ከሰራን ከህብረተሰቡ የሚሰውር ተጠርጣሪ የለም፡፡ የመረጃ አድማሳችን በማስፋትና የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማዳበር ተቀናጅተን መስራት ከቻልን ችግሮችን መቅረፍ እንደሚቻል ገልጸው በቀጣይ ጊዜያቶች አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል ሲል ሪፖርተራችን አበራ ተስፋየ ዘግቧል፡፡