Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

የዳያስፖራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊነትና ተግባር

  የክልሉ መንግስትበውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በክልላቸው በተለያዩ የልማት መስኮችየሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ሲሆን የሚደረገውን ድጋፍ ለማጠናከር እንዲቻል በርዕሰ መስተዳድርና ክልል መስተዳድር ም/ቤት ጽ/ቤትየዳያስፖራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እንዲደራጅ የተደረገሲሆን፡-

  ·ጽ/ቤቱ በዋናነት ለዳያስፖራው የመረጃ ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን ዳያስፖራው በክልሉ ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት የሚፈልጋቸውን የተለያዩ መረጃዎች  ከሚመለከታቸው ሴክተሮች በማሰባሰብ በቀላሉ እንዲያገኝ ማድረግና ድጋፍ መስጠት፣

  ·በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በክልላቸው ገጽታ ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግ፣

  · ዳያስፖራውን በተለያዩ የልማት መስኮች እንዲሳተፍ ለማስቻል የወጡ ፖሊሲዎችን ፤አዋጆችና ልዩ ልዩ መመሪያዎችን በማሰባሰብና በማደራጀት ዳያስፖራውና ሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች እንዲያውቋቸው ማድረግ፣

   በክልሉ በየሴክተሩ በተለያዩ የልማት መስኮች የሚሳተፉ ዳያስፖራዎችን መረጃ መያዝ፣ የደረሱበትን ደረጃ ማወቅ፤ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ መለየት፤

  ·         የክልሉ ተወላጅ ብቻ ሳይሆን ሌላም ዳያስፖራ በክልሉ ልማት እንዲሳተፍ ማበረታታትና መደገፍ፣

  ·         በክልሉ ያሉ የኢቨስትመንት ዕድሎች፣ ማትጊያዎችና መረጃዎች እንዲሁም በጥናት የተለዩ ኘሮጀክቶችን በሃርድና በሶፍት ኮፒ በማሰራጨት ለዳያስፖውማስተዋወቅ

  ·         በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው የሚመጡበትን ወቅት መሠረት በማድረግ በአገር አቀፍ ደረጃ ከሚደረጉ ስብሰባዎች ጎን ለጎን ክልል አቀፍ የሆነ በዓል በማዘጋጀት የክልሉ ተወላጆችን የማወያየት እንዲሁም በክልሉ በኢንቨስትመንት፣ በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በልገሳና በበጎ ፈቃደኝነት ወዘተ…ስራ በከፍተኛ ደረጃ ለተሳተፉና አረዓያ ለሆኑት ዕውቅና ለመስጠት ሽልማትና የምስክር ወረቀት መስጠት፣ እንዲሁም ማንነታቸውንና ያከናወኗቸውን በጎ ተግባራት የሚያሳዩ ጽሁፎችን በመጽሄት ላይ ማውጣት፤ እንዲሁም ዶክመንታሪ ፊልም አዘጋጅቶ በውጭ ያሉ ሌሎች የክልሉ ተወላጆች እንዲያውቁት ማድረግ

  ·የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከክልላቸው የዳያስፖራ አባላት ጋር ለመወያየት ወደ ውጭ ሀገር ሂደው በውይይቶቹ ወቅት ለዳያስፖራ አባላቱ ቃል የተገቡ ጉዳዮች በተግባር ስለመፈፀማቸው ክትትል ማድረግ፣

   በክልሉ የዳያስፖራውን ድጋፍ የሚሹ ከፍተቶችን /critical Gaps/ ለመለየት ጥናት ማካሄድ፣ ይህንን ክፍተት ለመሙላት በተለያዩ ኘሮግራሞች በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ለመሳተፍ ለሚመጡት ባለሙያዎች ኘሮግራሞችን ማዘጋጀት፣ ጉዳዩን መከታተል፣ ውጤቶቹን በመረጃነት መያዝ፣

  · ሴት ዳያስፖራዎችን ለማበረታታት ልዩ ትኩረት መስጠት፣ በየአካባቢያቸው የሴቶችን ችግር ለመፍታት እንዲንቀሳቀሱ ማትጋት፣ ከሴቶች ማህበራት ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ ማድረግ፣

  ·ከውጭ ቆይታ በኋላ ወደ ክልላቸው ተመልሰው የሚመጡ ዜጎች ጉዳዩ ከሚመለከተው የተለያዩ አካላት ጋር በመተባበርና በመቀናጀት ሊቋቋሙ፣ ራሳቸውን ለመምራትና ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ ወደሚያስችል ስራ ሊሰማሩ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በጽ/ቤቱ በኩል የመረጃና የምክር አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት፣

  · ዳያስፖራው ለቤተሰቡ የሚልከውን ገንዘብ ለዕለትና ጊዜያዊ ፍጆታ ከመዋል አልፎ ለልማታዊ ተግባር ጥቅም ላይ እንዲውል ለቤተሰቦቻቸው የምክር አገልግሎት መስጠት

  · በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውወር ምክንያት  ወደ ውጭ ሲወጡ እንግልት የሚደርስባቸውን የክልሉ ተዎላጆችን በተመለከተ ክትትል ማድረግና ከሚመለከታቸው ሴክተሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አስከፊነቱን ለሕዝቡ ማሳዎቅና ማስተማር፣

  · በክልሉ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ በመፍጠር በየጊዜው የዳያስፖራው ተሳትፎ ያለበትን ሁኔታ መገምገምና ዳያስፖራው ያጋጠሙትን ችግሮች ለይቶ ከፍተኛ አመራሩ እንዲያውቃቸው ማድረግና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የሚፈቱበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤

  · ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር ተቀናጅቶ መስራትና ከሁሉም ክልሎች የዳያስፖራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች ጋር የመረጃና የልምድ ልውውጥ ማድረግ፣