Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

የጽ/ቤቱ ሪፖርት

  በአብክመ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ

   የ2003 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

  በሃገራችን ብሎም በክልላችን መተግበር ላይ ያለዉን የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዉጤታማ ለማድረግ ከአስፈፃሚዉ አካል ከፍተኛ ርብርብ ይጠበቃል። በዚህም ሂደት በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችና የሚጠበቀዉን ልማት ለማፋጠን እንቅፋት የሚሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መከሰታቸዉ አይቀሬ ነዉ።

  እነዚህንና መሰል የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍና አስተዳደራዊ መፍትሄ ለመስጠት እንዲሁም መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና በተገልጋዮች ለሚነሱ ቅሬታዎች አፋጣኝ መፍትሄ ለመስጠት ይቻል ዘንድ ቅሬታዎች የሚቀርቡበት፤ የሚጣሩበትና አፋጣኝ ውሣኔ የሚያገኙበት ሥርዓት በክልላችን በደንብ ቁጥር 55/2000 በአዲስ መልክ ከተዘረጋ ጀምሮ ህብረተሰቡ በሥርዓቱ እየተስተናገደ ይገኛል።

  በዚህም መሠረት ለህብረተሰቡ የተፈጠረ ግንዛቤ፣ ለቅሬታ ማስተናገጃ አካሉ የቀረቡ ጉዳዮችና የቅሬታዎች መንስዔ የዚህ ሪፖርት ይዘት ዋነኛ አካል ሆነው ቀርበዋል።

  የቅሬታ ማስተናገጃ ሥርዓቱ ዓላማዎች፦

  የምናከናውናቸው ተግባሮች የቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓቱን ዓላማዎች ለማሳካት ስለሆነ የዚህን ስርዓት ዓላማ፣ ተግብርና ኃላፊነቶችን ማስተዋወቅ ተገቢ ነው። በዚህ መሰረት የደንቡ ዓላማዎች

   • በመንግስት መ/ቤቶች ውስጥ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና አስተዳደራዊ በደልን መከላከል፣
   • የአገልግሎት አሰጣጥን በተከታታይ ለማሻሻል የተገልጋዮችን እርካታ ለመጠበቅ የሚረዱ መረጃዎች ምንጭ ሆኖ የማገልገልና ለተጠቃሚዎች አለመርካት መንስኤ የሆኑ ስህተቶችን ማረም፣
   • በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ካለመርካት በተገልጋዮች የቀረቡ ቅሬታዎችን አፋጣኝ ምላሽ መሥጠት፣
   • መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አኳያ የሚያጋጥሙ ችግሮችና መንስኤዎችን በማወቅ እንዲወገዱ ማድረግ፣

  አጠቃላይ ሪፖርቱን ለማየት ይህን ሊንክ ይጫኑ