Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

                                 

የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዋች ቡድን የመስክ ስራ  ጉብኝት አደረጉ

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዋች  ቡደን በምስራቅ አማራ  ሰሜን  ሽዋ ዞን በተመረጡ 5ወረዳዋች እና 11ቀበሌዋች ከታህሳስ 13/2007 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት  የመስክ ክትትል እና  ቁጥጥር  ተግባር አከናውኗል፡፡ ቡድኑ  በመስክ  ምልከታው  የግሽ ራቤል፤ አንጾክያ ገምዛ ፤ ኤፍራታና ግድም፤ ቀወት እና ሲያደብር እና ዋዮ  ወረዳዋችን አጠቃላይ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዋች ተዘዋውሮ  ተመልክቷዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴዋች ቡድን  በመስክ ጉብኝቱ  ካተኮረባቸው ጉዳዮች ውሰጥ  በግብርና የመኸር ሰብል አሰባሰብ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ፤ የመስኖ ልማት ስራ እንቅስቃሴ፤ የተፈጥሮ ሃብት  ቅድመ ዝግጅት ስራ ምን ላይ እንዳለ ፤የትምህረት የጤና  እና ሌሎች ተግባራትን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡

ቡድኑ ባያቸው ተግባራት ዙሪያ ከቀበሌ፤ ከወረዳ እና የዞን አመራሮች ጋር በየደረጃው ውይይት አድርጓል፡፡ በውይይቱም ወቅት በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ  በእጥረት የታዩ ጉዳዮች እንዲስተካከሉ  ለሚመለከታቸው አካላት አሰተያቱን ሰጥቷል፡፡ በመጨረሻም ከቀበሌ ፤ ከወረዳ እና ከዞን አቅም በላይ የሆኑ ችግሮችን ከሚመለከታቸው የክልሉ ቢሮዋች ጋር ለመምከር ጥያቄዋችን በመቀበል የመስክ ምልከታውን አጠናቋል፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት  የተዋረድ ምክር ቤቶችን የ2007 ዓ.ም  የመጀመሪያ  ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገውን  በወልደያ ከተማ አካሄደ፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት  አመራሮች እና ሰራተኞች ህዳር 29 ‹‹በህገ-መንግስታችን  የደመቀ  ኢትዮጲዊነታችን  ለህዳሴያችን›› በሚል መሪ ቃል ለ9ኛ ጊዜ  የተከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች በዓል በፓናል ውይይት አከበሩ፡፡

የአብክመ የኦዲት ግኝት ክትትል ግብረ ሃይል የ2006 እቅድ አፈፃፀም ዓምገማ እና የ2007 ዓ/ም ዕቅድ ትውውቅ መድረክ

የአማራ ክልል ምክር ቤት እና የባህርዳር ከተማ ኑዋሪዎች ለ9ኛው የብሔር ብሄርሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ለመታደም ወደ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ለሚጓዘው ለአፋርና እና ለትግራይ ክልል የኪነት ቡድን አቀባበል አደረጉ፤

የክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች 26ኛውን የዓለም ኤድስ ቀን በፖናል ውይይት አከበሩ፤

የበዓሉ መሪ ቃል “አንድም ሰው በኤች አይቪ እንዳይያዝ ቃል እንገባለን”

የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች  በዓልን ምክንያት በማድረግ  ጋዜጣዊ መግለጫ ተሠጠ

9ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሠቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማ “በህገ- መንግስታችን የደመቀ ኢትዮጵያዊነታችን ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል በድምቀት የሚከበር  መሆኑን የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ያለው አባተ ገለፁ፡፡

 አፈ-ጉባኤው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ህዳር29 በየዓመቱ  የሚከብረው የአዲስቷ ኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የፀደቀበት ቀን በመሆኑ ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለህገ መንግስቱ የገቡትን ቃል ኪዳን በየጊዜው እያደሱ እንዲሄድና ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ህገ መንግስቱን ለማስተማር እና ለማሳወቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ክልላችን በበዓሉ በተሳታፊነት ከመካፈሉም በላይ  ወደ በዓሉ የሚሄዱ የአፋር እና የትግራይ ክልል የባህል ቡድን አባላት በሚያርፉባቸው በክልላችን ከተሞች  አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት የተደረገ መሆኑን የተከበሩ አቶ ያለው አባተ  አብራርተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ ካሉ ሁሉም  ብሔረሰቦች የተውጣጣ የባህል ቡድን    ለ

ልምምድ ሲያደርግ ቆይቶ በዓሉ ወደ የሚከበርበት ቦታ ለመጓዝ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በሌላም በኩል በልማትና በመልካም አስተዳደር መስኮች ክልሉ ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ የሚያሳይ የልማት ኤግዚቪዥን ለማቅረብ በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት አስተባባሪነት ዝግጅቱ ሲደረግ ቆይቶ ሥራው የተጠናቀቀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

 ከዚህ በተጨማሪ በክልላችን በሁሉም ቦታዎች በዓሉ በፖናል ውይይት፣ በህገ መንግስት ጥያቄና መልስ ውድድር እንዲሁም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ እንደሚውል አፈ ጉባኤው በመግለጫቸው አብራርተዋል፡፡

9ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በዚህ ዓመት ሲከበር ከሌሎች ጊዜያቶች ልዩ የሚደደርገው በዓሉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኘሮጀክት ግንባታ እየተሠራ ባለበት ክልል መከበሩ ነው፡፡ ይህም መሆኑ በበዓሉ ላይ ለመታደም የሚሄደው ህዝብ  የህዳሴ ግድብ ኘሮጀክት ያለበትን ሁኔታ ይጐበኛል በዚህ አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ውስጥ ሆነው ግንባታውን የሚሰሩ አካላትን ያበረታታል፡፡አጋርነቱንም ያስመሰክራል ፡፡ ጉብኝቱም የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሰለሚኖረው ህዝቡ በቀጥታ ፕሮግራሙን ይከታተላል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ ይህም ለኘሮጀክቱ ቀጣይ የሥራ እንቅስቃሴ ለሚደረገው የህዝብ ድጋፍ ጠቀሜታው የጐላ መሆኑን  አፈ ጉባኤው አብራርተዋል፡፡

 በመጨረሻም የክልሉ ህዝብ በየአለበት አካባቢ  በሚዘጋጁ ሁነቶች በመሳተፍ በዓሉን እንዲያከብር እና ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ ግንባታ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሣስባለሁ ብዋል ፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት የ2007 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማውን አካሄደ፡፡

ሴት የወረዳ ምክር ቤት አባላትን የንግግር ክህሎት ለማሳደግ የሚስችል ስልጠና ተሰጠ፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት ከምክር ቤቶች አቅም ግንባታ ፕሮጀክት (helvatase erthiopia) ጋር በመተባበር በክልሉ በሚገኙ ፕሮጀክቱ ባቀፋቸው 4 ወረዳዎች ለሚገኙ ደቡብ አቸፈር፡ሜጫ፡ ደራ እና ፎገራ ወረዳ ለተመረጡ ሴት የወረዳ ምክር ቤት አባላት የመድረክ ላይ ንግግር ክህሎትን ለማሳደግ የሚስችል ስልጠና በተቋሙ ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሰጠ፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት ከምክር ቤቶች አቅም ግንባታ (helvatase erthiopia) ጋር በመተባበር የአመራርነት ክህሎትን ለማሳደግ የሚያስችል ስልጠና ለሜጫ እና ለደቡብ አቸፈር ወረዳ አመራሮች ለ3 ተከታታይ ቀናት በዳንግላ ሀሁ ሆቴል ስልጠና ተሰጠ፡፡

 

የታላቁ  የኢትዮጵያ  ህዳሴ  ግድብ  ዋንጫ  አቀባበል  እና  የመሸኘት   ስነ-ሥርዓት   በአማራ  ብሔራዊ  ክልል  ምክርቤት  አዳራሽ  በደመቀ   ሁኔታ  ሲከበር ፡፡

v7 ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ምክንያት በማድረግ መስከረም 30/2007 ዓ.ም በክልል ምክርቤት ጽ/ቤት አመራሮች አና ሰራተኞች የተደረገ የፓናል ውይይት፡፡       

v7 ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ምክንያት በማድረግ  ጥቅምት 2ቀን 2007 ዓ.ም በክልል ደረጃ  በ ሙሉዓለም የባህል ማዕከል  የተካሄደ  የፓናል  ውይይት፡፡

v7 ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን  ‹‹በህዝቦቿ ትጋትና ተሳትፎ ድህነትን ድል በመንሳት ብሔራዊ  ክብሯንና ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ያለች ሃገር ! ኢትዮጵያ! ›› በሚል መሪ ቃል  በበህረዳር ከተማ  ሚሊኔየም አደባበይ የመንግሰት ከፍተኛ አመራሮችና  የከተማው ህዘብ በተገኘበት በዓሉ በደመቀ ሁኔታ ሲከበር፡፡