Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

የአማራ ክልል ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴዎች ቡድን በምስራቅ አማራ በዋግ ኸምራብሄረስብ አስተዳደር ፣ በሰሜን ወሎ እና በደቡብ ጐንደር አስተዳድር  ዞኖች  በተመረጡ አራት ወረዳዎች  ማለትም አበርገሌ፣ ቆቦ ና ነፋስ መውጫ  ከተማ አስተዳደር እና ላይ ጋይንት ወረዳ የአስፈፃሚ አካሉን የ2007 በጀት ዓመት የ6 ወራት የልማትና የመልካም አስተዳደር የእቅድ አፈፃፀም ተመለከተ፡፡ የቋሚ ኮሚቴዎች ቡድን  ከጥር 17 – 25/2007 ዓ/ም ባካሄደው የመስክ ምልከታ ትኩረት ያደረገው የተፈጥሮ ሃብትእ ንክብካቤ ሥራን፣ የነባር እና የአዲስ የመስኖ ስራ  አፈፃፀም፣  ተማሪዎችን የማብቃትና የማቋረጥ እንዲሁም በጥቃቅንእና አነስተኛ የተደራጁ ወጣቶች የተፈጠረላቸው የስራ መስክ ላይ ነበር፡፡

 

የቋሚ ኮሚቴዎች ቡድን በአራቱ ወረዳዎች በተመረጡ 8 ቀበሌዎች ላይ በመውረድ የተመለከተው የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም አበረታች መሆኑን  ከህዝብ ጋር ባደረገው ውይይት አረጋግጧል፡፡ በየደረጃው ከሚገኙ አስፈፃሚ አካላት  ጋርም ውይይት አድርጓል፡፡ በዚህም ውይይት የታዩ ጠንካራ ጐኖች እንዲበረታቱ የተከሰ እጥረቶችም በቀጣይ ስድስት ወር እንዲስተካከሉ አስተያየት ሰጥቷል መግባባት ላይም ተደርሷል ፡፡