Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

የባለስልጣኑ ሰራተኞች 23 ኛውን የግንቦት 20 በዓል በደማቅ ሁኔታ አከበሩ

  የአማራ ገቢዎች ባለስልጣን ሰራተኞች የግንቦት 20ን 23ኛ በዓል ከዋዜማው ጀምረው እስከ ግንቦት 23 2006 ዓመተ ምህረት ድረሰ በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።


  "ሩቅ አስባ ሩቅ ለማደር እየተጋች ያለች ሀገር" በሚል መሪ ቃል የተከበረው በዓል ዘንድሮ በተለየ ሁኔታ የግንቦት 20 ፍሬዎችን በሚያሳይ በደማቅ ሥነ-ስርዓት ነው። በዕዝ ኢኮኖሚ ተጠፍንጎ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ አላሰራ ብሎ የነበረው የደርግ መንግስት ድል ከተመታበት ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓመተ ምህረት በኋላ መላው ህዝብ እንደ አቅሙና ፍላጎቱ ያለውን ሃብት አሟጦ መስራት የሚያስችል ሁኔታ ስለተፈጠረለት አያሌ ባለሀብቶች ተፈጥረው ቢሊየነር መሆን ችለዋል። በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮች በመፈጠራቸውም በአገራችን ዘርፈ ብዙ የስራ መስኮች ተፈጥረዋል። በርካታ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ወጣቶች የኢንደስትሪ ሽግግር አካሂደዋል። በርካታ አርብቶ አደሮች ወደ አርሶ አደርነት ተሸጋግረው በጓሯቸው እሸት መቅመስ ችለዋል። እነዚህ እና ሌሎች የስራ አማራጮች በመበራከታቸው የአገሪቱ የውስጥ ገቢ እያደገ እና እያደገ ይገኛል።


  አገራችን ከብድርና ከእርዳታ ተላቃ በራሷ ገቢ መተዳደር የምትችለው በርካታ ስራ ፈጣሪ ቢሊየነሮች ሲበራከቱ በመሆኑ በዚህ ዘርፍ ለሚሰማሩ ልማታዊ ስራ ፈጣሪዎች የአገር ውስጥና የውጭ አገር የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ፍትሃዊ የቀረጥ አጣጣል ዘዴ በመጠቀም የገቢና ወጭ ምርቶችን ለማጣጣም ጥረት እየተደረገ ይገኛል።


  የባለስልጣኑ ሰራተኞች የዘንድሮውን በዓል ያከበሩት በተለያየ ሁኔታ ሲሆን የመጀመሪያው በሙሉአለም የባህል ማዕከል ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት የተውጣጡ የመንግስት ሠራተኞች ጋር በፓናል ውይይት በመሳተፍ ነው። ውይይቱ በቅድመ እና ድህረ 1983 የነበሩና ያሉ እውነታዎች የተዘከሩበት በርካታ አስተያየትና ጥያቄዎች የተስተናገዱበት እና የጋራ መግባባት የተፈጠረበት መድረክ ነበር። በመቀጠል በዕለቱ ግንቦት 20 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት ከባለስልጣኑ መስሪያ ቤት በመነሳት ባህር ዳር ሁለገብ ስታዲየም ድረስ ስርዓት በተሞላበት ሁኔታ መሪ ቃሎችን በማስተጋባት፣ ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብና ቀስቃሽ መዝሙሮችን በማሰማት በሰላማዊ ሰልፍ ተከብሯል።


  በመጨረሻም ከግንቦት 20 ፍሬዎች መካከል የጣና ፍሎራ አበባ ማምረቻ ኢንቨስትመንት ግንቦት 23 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት የተደረገው ጉብኝት ልማትና ዕድገቱን በተግባር ማረጋገጥ የተቻለበት ነበር። የጣና ፍሎራ አበባ ማምረቻን በአካል እንዳየነው የአበባ ምርት እንዲህ በብዙ ዘመናዊ መሳሪያዎች ታግዞ ለውጤት እንደሚበቃ በዓይኑ ላላየ ቢነግሩት አያምንም። ይሀ የኢንቨስትመንት ዘርፍ በክልላችን ፈር ቀዳጅ የአበባ ማምረቻ ከመሆኑ በተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ብዙ ቋሚና ጊዜያዊ ሰራተኞችን ቀጥሮ የስራ ዕድል እንዲያገኙ ያደረገ ለባህር ዳር ከተማና አካባቢው ወጣቶች ባለውለታ ነው። ከግንቦት 20 ፍሬዎች ከተለያዩ የገቢ ዘርፎች የሚሰበስበው ገቢ ከዓመት ዓመት እድገት እያሳየ የሚገኝ በመሆኑ በቀጣይም በድህነት ላይ የሚደረገውን ዘመቻ በማስፋት በክልላችን የእርሻና ኢንዱስትሪ አማራጮችን በማጠናከር ከግብር እና ታክስ በሚሰበሰበው ገቢ አስተማማኝ የእድገት መሠረት መጣል እንደሚቻል አንዳንድ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

ለጋዜጠኞች ስልጠና ተሰጠ

  የአማራ ገቢዎች ባለስልጣን በገቢ ግብር አዋጅ ደንቦችና መመሪያዎች አፈጻጸም ዙሪያ ለአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ጋዜጠኞች ከግንቦት 2 እስከ 3 2006 ዓ/ም ለሁለት ቀናት በዳንግላ ከተማ ያዘጋጀው ስልጠና ተጠናቀቀ።

  በገቢ ግብር አዋጁ ዙሪያ ለጋዜጠኞች ስልጠና መስጠት ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት በክልላችን ፍትሃዊ፣ ዘመናዊና ቀልጣፋ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የብዙሃን መገናኛ ተቋማት ተሳታፊ እንዲሆኑና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ፍትሃዊ የህዝብ ተደራሽነት ስራ መስራት የሚችሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ነው። ስልጠናው በባለስልጣኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የተሰጠ ሲሆን በገቢ ግብር አዋጁ ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ የቀረበበት ነበር።

  ባለስልጣኑ መሰል ስልጠናዎችን ለአጋርና ባለድርሻ አካላት እንዲህ በተደራጀ ሁኔታ የስልጠና ሰነድ በማዘጋጀት ለየት ባለ ሁኔታ ሲሰጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢሆንም ለፍትህ አካላት፣ ዳኞችና አቃቤ ሕጎች በገቢ ግብር አዋጁ አተገባበር በ2005 ዓ.ም የአንድ ቀን ስልጠና መሰጠቱ የሚታወስ ነው።
  በስልጠና የተሳተፉ በቁጥር 70 የሚሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናው የዘገየ ቢሆንም አስፈላጊ መሆኑን፣ ለስራቸው አጋዥ እንደሚሆንላቸውና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ዘገባ ለመስራት እንደሚያስችላቸው ገልጠዋል። ከግብር ጽንሰ-ሀሳብና አተገባበር አኳያ ባለስልጣኑ ተከታታይ የእውቀትና ክህሎት ግንባታ መስጠት የሚያስፈልገው በመሆኑ የራሱ የሆነ የቴሌቪዥን፣ የሬዲዮና የጋዜጣ የአየር ሰዓትና ዓምድ ሊኖረው ይገባል፡፡ ለዚህም ከሚመለከታቸው አመራሮች ጋር በመምከር ነጻ የአየር ሰዓት እንዲኖረው ማድረግ ተገቢ መሆኑንም ጠቁመዋል።

  ከህብረተሰቡና ከራሳቸው የታዘቧቸውን አስተያየትና ጥያቄዎች ከባለስልጣኑ፣ ከህብረተሰቡና ከብዙሀን መገናኛ ተቋማት ምን ይጠበቃል? እንዴትስ በጋራ መስራት ይቻላል? ባለስልጣን መ/ቤቱንና ግብር ከፋዮችን እንዴት ማቀራረብና ፍትሃዊ የግብር አስተዳደር ስርዓት ማስፈን ይቻላል የሚሉ ጉዳዮችን በማንሳት በሰፊው የተወያዩ ሲሆን ላነሷቸው ጥያቄዎችም ተገቢውን ምላሽ አግኝተዋል።
  በስልጠናው ማጠናቀቅያ ዕለት የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አስማማው ማሩ ከብዙሀን መገናኛ ተቋማት ጋር የምናደርገውን ተመሳሳይ ስልጠና በማስፋት በቀጣይ ለሌሎችም የብዙሀን መገናኛ ተቋማትና ጋዜጠኞች ተከታታይ የስልጠና መድረኮች እንደሚዘጋጁ እና የብዙሀን መገናኛ ተቋማትም ባለስልጣኑ በሚያደርጋቸው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች እስካሁን ያልተለዩን ቢሆንም በቀጣይ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ ልማታዊ ጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር በመላበስ የባለስልጣኑን ዓላማ፣ ስልጣንና ተግባር በመረዳት አሰራራችንን ቀልጣፋና ፍትሃዊ ለማድረግ በምናደርገው ጥረት እንዳትለዩን በማለት በራሳቸውና በባለስልጣኑ ስም መልዕክት አስተላልፈዋል።

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ተጠቃሚዎች ቁጥር እያደገ ይገኛል፡፡

  በአማራ ገቢዎቸ ባለስልጣን በ2006 በጀት ዓመት በ35 ከተሞች ደረጃ “ሀ” 2236 ደረጃ “ለ” 4035 ድምር 6271 ግብር ከፋዮችን የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ ተይዞ በ41 ከተሞች ደረጃ “ሀ” 1034 ደረጃ “ለ” 310 ድምር 1361 ተጠቃሚ ሲሆኑ ከመስከረም 2004 እስከ መጋቢት 30/2006 ዓ.ም የደረጃ "ሀ" እና ደረጃ "ለ" የሽያጭ  መመዝገቢያ መሳሪያ የገዙ ግብር ከፋዮች ብዛት በድምሩ 4028 የደረሰ ቢሆንም ክልሉ ካለው የደረጃ "ሀ" እና ደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ብዛትና ዕቅድ አንጻር ዝቅተኛ ነው። ይከውም፤ በ2004 እና በ2005 ዓ.ም ደረጃ "ሀ” ደረጃ "ለ” ድምር 2,667 በ2006 ዓ.ም ደረጃ "ሀ" 1034  ደረጃ "ለ" 318 ድምር 1361 ጠቅላላ ድምር 4028 ብቻ መሆኑን ከሽያጭ መመዝገቢያ  መሳሪያ አስተባባሪ የተገኘ መረጃ ያሳያል።