Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

የግብር ትምህርትና ኮሙኒኬሽን ዋና የሥራ ሂደት

  የመረጃ ቴክኖሎጂ  በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣት አለምን ወደ አንድ መንደር እየለወጠ ባለበት በአሁኑ ወቅት የመንግሥት መ/ቤቶች የተለመደና ኋላቀር አሰራርን በመከተል የተቋቋሙበትን ዓላማ በተፈለገው ፍጥነትና ጥራት ለማሳካትም ሆነ የደንበኞችን ፍላጐት ለማርካት ፍጹም የማይታሰብ ነው፡፡ በመሆኑም የነባሩን አሰራር ክፍተቶች በመለየት፣ የነባሩ ታሳቢዎችን በመስበርና በጥራት ተደራሽ ግቦችን በማስቀመጥ በተጨማሪም የተለያዩ የግብር ትምህርት መስጫ መንገዶችና የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ለደንበኞች አስፈላጊውን ትምህርትና መረጃ በመስጠት በግብር አስተዳደር ሥርዓቱ ላይ ያለውን ሥር የሰደደና የተሳሳተ አመለካከት በመቀየር ጤናማና ውጤታማ የግብር አስተዳደር እንዲኖር የሚያስችል የግብር ትምህርትና ህዝብ ግንኙነት የሥራ ሂደት ተቀርጿል፡፡

   

  ዋና ዋና ተግባራት

  1.   የግብር ትምህርትና ህዝብ ግንኙነት ዕቅድ ማዘጋጀት፣
  2.  የስልጠና ፍላጐት ክፍተቶችን መለየት፣
  3.  ስልጠና መስጠት፣
  4.  የሚኒ ሚዲያና የጥያቄና መልስ ውድድር ማዘጋጀት፣
  5.  የህትመት መረጃ ማቴሪያል ማዘጋጀትና ማሰራጨት፣
  6.  የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ መረጃ ማዘጋጀት፣
  7.   የገጽ ለገጽ /የቃል መረጃ/ ማዘጋጀት፣
  8. በሁሉም ዓይነት መሳሪያዎች /የግንኙነት አግባቦች/ ሊተላለፉ የሚችሉ ማቴሪያሎችን ማዘጋጀት፣
  9. የቤተ መጽሐፍት አገልግሎት መስጠት፣
  10. የኦዲዩቪዥዋል መረጃ ማዘጋጀት፣