Web Content Display Web Content Display

Minimize Maximize

የገቢ አሰባሰብና ክትትል ዋና የሥራ ሂደት

     የክልሉ መንግሥት ለኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንዲሁም ለመልካም አስተዳደር ሥራ ማስፈጸሚያ የሚውል ገንዘብ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ከህብረተሰቡ በግብርና ታክስ መልክ መሰብሰብ እንዳለበት ይታወቃል፡፡ ግብርንም ሆነ ታክስ ለመሰብሰብ ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ከመንግሥት ወይም ከገቢ አስገቢው /ከአገልግሎት ሰጪው/ መ/ቤት የሚጠይቀው በጥራት፣ በፍጥነት፣ ከተጨማሪ ወጪ የፀዳ ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት ማግኘት ነው፡፡ በመሆኑም በአንድ ከተማ የሚገኙ ግብር ከፊዮች በተለያየ አካል በተለያየ ጊዜ ግብር እንዲከፍሉ መጠየቁ ግብር ከፋዮችን ያንገላታ ስለነበር አገልግሎት አሰጣጡ የደንበኞችን ፍላጐት የሚያረካና የግብር ከፋዮችን ድካም በሚቀንስ አግባብ የገቢ አሰባሰብና ክትትል አዲስ የሥራ ሂደት ተቀርጿል፡፡

   

  ዋና ዋና ተግባራት

  1. የክፍያ ጊዜ ገደብ በመወሰን ገቢን መቀበል፣
  2.   ገቢን ማስታወቅና መሰብሰብ፣
  3.  በግብር/ታክስ ውሳኔ ላይ የሚቀርቡትን ቅሬታ በመመርመር ማጽደቅና ውሳኔውን ለግብር ከፋዩ ማሳወቅ፣
  4. ያልተሰበሰበ ግብርና ታክስ ክትትል ማድረግ፣
  5. በሚቀርበው የተመላሽ ጥያቄ መሠረት አረጋግጦ ተመላሽ ክፍያ መፈጸም፡፡